Song Lyrics

አያይዘን

አያይዘን አንድ አድርገን እንዳንጠፋ ተነካክሰን ቃየን ወንድሙን ገደል ጌታ መስዋዕቱን ስላልተቀበለ ልቡ በቅናት ተሞልቶ ለጥፋት ተነሳ ጭካኔ ተሞልቶ ዛሬም እንደ ቃየን አለ እንደገና ለምን ተሳካለት ብሎ የሚቀና ሰይፍ ይዟል በእጁ አፉ እንደማር ጉድጓድ ይቆፍራል ገድሎ ሊቀብር አያይዘን አንድ አድርገን እንዳንጠፋ ተነካክሰን ከሁሉ መጀመሪያ የታዘዝኩት ፈቃድ እንኳን ወንድሚንና ጠላቴን እንድወድ እጃችን ተያይዞ ልባችን ተራራቀ ከየት ፈውስ ይመጣል መርዙ ከተደበቅ አያይዘን አንድ አድርገን እንዳንጠፋ ተነካክሰን በቤትህ ውድድሩ በዛ እኔ ልታይ ልታይ እኔ ብቻ ልግዛ ቃልህን የሚሰብከው ሞልቶ እንደሚናገረው ይሚኖረው ጠፍቶ ነብይ አስተማሪ ሁሉ ጐራ ይዞ ሰይፍ ይማዘዛል እዛ እዚህ ማዶ አካል ተበታትኖ ዓይኖረውም ውበት ማን ክብርህን ወስዶ ይኖራል በሕይወት አያይዘን አንድ አድርገን እንዳንጠፋ ተነካክሰን ከሁሉ መጀመሪያ የታዘዝኩት ፈቃድ እንኳን ወንድሚንና ጠላቴን እንድወድ እጃችን ተያይዞ ልባችን ተራራቀ ከየት ፈውስ ይመጣል መርዙ ከተደበቅ የህግ ሁሉ ፍጻሜ የትዛዛትም ሁሉ መጀመሪያ ባልንጀራህን እንደ እራስህ አድርገህ ውደድ ብለኸን የቤትህ ማገርና መሰሶ የሆነውን ፍቅርን ጥለን ፍቅርን ስንገፋት ስትወጣ ከቤቷ እግሯን ተከትሎ ገባ ያ ጠላቷ ማናከስ ጀመረ እንድንጠፋፋ አደባባይ ወጥተን እንድንገፋፋ ሰው አካሉን መብላት መንከስ ከጀመረ መገመት ይቻላል ምን ሊሆን እንዳለ አወይ ጉድ ሆነናል ወገን ተው እንንቃ ፍቅር በሊለበት እርሱም የለም ለካ አያይዘን አንድ አድርገን እንዳንጠፋ ተነካክሰን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection