Song Lyrics

የመዳኔ ነገር

ደግሜ ደግሜ ብደጋግም የማይሰለቸን ሁሌ ብዘምር አሁንም መልሼ ብደጋግም የማይሰለቸኝ ሁሌ ብዘምረ የመዳኔ ነገር ቀሎ ስለመጣ አይቀልም በሕይወቴ የመስቀሉ ስራ በክብር ታጅቦ ይመጣል ሊወስደኝ እርጐኛል ሙሽራ ሰማይ ደስታ ሆነ ዕልልታው ቀለጠ በእኔ መዳን እንዴተ መታደል ነው በበጉ ዙፋን ፊተ ከእርሱ ጋር መሆን አጋንንት ቢወጣ ሽባ ቢተረተር የሞተ ቢነሳ ይህም ያልፋል ምድር አይወዳደርም ይሄኛው ተአምር የመዳኔ ነገር ደግሜ ደግሜ ብደጋግም የማይሰለቸን ሁሌ ብዘምር አሁንም መልሼ ብደጋግም የማይሰለቸኝ ሁሌ ብዘምረ የመዳኔ ነገር አማኝ ሞት አይፈራ እንግዳ ነውና በዚህ ምድር ላይ ይናፍቃል እንጂ ከአምላኩ ጋር መኖር በላይ በሰማይ ሰው ዓለምን ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጐድል መቼ ይጠቅመዋል ከክርስቶስ ጋራ ለዘላልም መኖር ከሁሉም ይበልጣል ጠላቴ ሆይ ስማ ሞኝህን አሰፈራራ ሞት እይፈራም አማኝ ሰማይ የእርሱ ስፍራ ይሄ አለኝ ብዬ ቁሳቁስ አልቆጥር የእኔ ሃብት ይሄ ነው ሞትን የሚሻገር የመዳኔ ነገር ክብር ቢሆን ያልፋል ዝና ቢሆን ያልፋል ጉልበት ቢሆን ያልፋል ሃዘን ቢሆን ያልፋል ማግኘት ቢሆን ያልፋል ማጣት ቢሆን ያልፋል የማያልፈው አንድ ነገር በሰማያት ያለ ክብር ተጽፎልኝ ስሜ በላይ ከዚህ በላይ ደስታ አለ ወይ በዚህ ነው የእኔ ደስታ ሞልቶኛል ዕልልታ ለዚህ ነው ጩኸቴ ሰማይ ቤት በመግባቴ ክብር ቢሆን ያልፋል ዝና ቢሆን ያልፋል ጉልበት ቢሆን ያልፋል ሃዘን ቢሆን ያልፋል ማግኘት ቢሆን ያልፋል ማጣት ቢሆን ያልፋል የማያልፈው አንድ ነገር በሰማያት ያለ ክብር ተጽፎልኝ ስሜ በላይ ከዚህ በላይ ደስታ አለ ወይ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection