Song Lyrics

ይሄ ነው የገባኝ

ውሰድልኝ ዛሬ ከነፍሴ የሆነ አምልኮዬን አላገናኘውም ከሁኔታ ጋራ ዝማርዬን ተላንት አመስግኜ ዛሬን አላማህም እንዲህ ብዬ ይጨምራል እንጂ አላሳንሰውም ምስጋናዬ የማየው ነገር ከምስጋናዬ አያግደኝም የምሰማው አንተን ከማምለክ አያስቆመኝም ምድረበዳዬን አለምልሞታል እያየ አይኔ በህሩን ከፍሎ ያሻግረኛል አምናለሁ እኔ ይሄ ነው የገባኝ ዝም ብሎ መዘመር ሁኔታው እያለ እግዚአብሔርን ማክበር (፪) የለመንኩትን የጠየኩትን ጥያቄ ሁሉ ከምስጋና ጋር እጠብቃለሁ አምኜ ቃሉን የከበደኝን ሸክሜን ሁሉ በእርሱ ላይ ጥዬ በአንዳች ነገር አልጨነቅም አለ ጌታዬ ይሄ ነው የገባኝ ዝም ብሎ መዘመር ሁኔታው እያለ እግዚአብሔርን ማክበር (፪) ደመና የለም አይታየኝም በዓይኔ ነፋሥም የለም አይታየኝም በዓይኔ ሳላይ አምናለሁ እንዲሀ ይሆናል ባዶ ሸልቆ ውኃ ይሞላል ይሄ ነው የገባኝ ዝም ብሎ መዘመር ሁኔታው እያለ እግዚአብሔርን ማክበር (፪) ምስክር ነኝ እኔ ምስክር ነኝ እኔ አይቻለሁኝ ሲሰራ ምስክር ነኝ እኔ ምስክር ነኝ እኔ ክንደ ብርቱ ነው ኃይለኛ ምስክር ነኝ እኔ ምስክር ነኝ እኔ ድንቅ ነው ተአምረኛ ምስክር ነኝ እኔ ምስክር ነኝ እኔ አይቻለሁኝ በዓይኔ ምስክር ነኝ እኔ ምስክር ነኝ እኔ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection