Song Lyrics

ከኖሩማ

ንፋሱ ነፈሰና አለፈ ወጀቡም ጸጥ አለ አለፈ መንገዴን ዞር በዬ ሳየው ይህ ሁሉ ለመልካም የሆነው ስላለ ጌታ አጠገቤ ስላለ አባ አጠገቤ ከኖሩማ ኑሮ ከአንተ ጋራ በችግር ቢሆን በመከራ ከተያዘም እጄ በአንተ እጅ ሕይወቴ ሰላም ነው የሚመች ስሄድ ከአንተ ጋራ በሕይወት መንገድ ምንም ነገር አይሆን ያለ አንተ ፈቃድ አያስጨንቀኝም ነገ የሚሆነው የነፍሴ ፍጻሜ በእጅህ ነው የእኔ ነገር ሰው ይማይዘጋው ሰው የማይከፍተው ሁሉ በእጁ ነው የእኔ ነገር መጀመሪያዬ መጨረሻዬ በእርሱ አይደል ወይ ከኖሩማ ኑሮ ከአንተ ጋራ በችግር ቢሆን በመከራ ከተያዘም እጄ በአንተ እጅ ሕይወቴ ሰላም ነው የሚመች ሲጸልይ ዳናኤል አንተን ስለጠራ ጉድ ጓድ ውስጥ ከተቱት በአንበሳ እንዲበላ ይንከባከቡታል እንኳን ሊበሉት ችግር ይቀየራል በምቾት የእኔ ነገር ሰው ይማይዘጋው ሰው የማይከፍተው ሁሉ በእጁ ነው የእኔ ነገር መጀመሪያዬ መጨረሻዬ በእርሱ አይደል ወይ ቆይ ምን አለ ከአንተ የራቀ የተሰወረብህ እኮ ምን አለ አልፋ ኦሜጋ ሁሉን የምታውቅ ቆይ ምን አለ ድንገት ተገልጦ የሚያስደነግጥህ እኮ ምን አለ ሰማይ ምድሩን ሁሉን በእጅህ ይዘህ መላ ሕይወቴ አምላኬ ሁሉ በእጅህ እድሜ ዘመኔ አምላኬ ሁሉ በእጅህ ነገዬም ቢሆን አምላኬ ሁሉ በእጅህ እስትንፋሴ እንኳን አምላኬ ሁሉ በእጅህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection