ሚነጋ አይመስልም ሌሊቱ ረዝሞ ጨለማውን አይቶ ሌሊቱም ያልፋል ደግሞም ይነጋል ብርሃን ተክቶ አይዘኝ ሃሳብ ትካዜ ይሆናል ሁሉ በጊዜ ( 2x) አትጠጉት በቃ ድንጋይ አድርጉበት ሸትቷል መቃብሩ ጠብቀነው ነበር በጊዜ እንዲመጣ አክትሟል ነገሩ ሰው ደክሞት ሲጨርስ ኢየሱስ እርሱ ይጀምራል በሞተ ነገር ላይ ይፈርዳል ሕይወት ይሰጠዋል ዝምታው ቢያስገርም የማያይ ቢመስልም አይቸኩል እንደ ሰው ይፈርዳል በጊዜው ታማኝ ነው ታማኝ ነው ሚነጋ አይመስልም ሌሊቱ ረዝሞ ጨለማውን አይቶ ሌሊቱም ያልፋል ደግሞም ይነጋል ብርሃን ተክቶ አይዘኝ ሃሳብ ትካዜ ይሆናል ሁሉ በጊዜ ( 2x) ልቧ ያዘነባት ሁሌ ምታለቅሰው ልጅ የሌላት ሃና ታሾፍባት ነበር ነገ የሚሆነው ያልገባት ፍናና በጊዜው ፈረደ አምላኳ እንባዋን አበሰ ትውልድ የሚያወሳው ልጅ ሰጣት ሕይወቷ ተካሰ ዝምታው ቢያስገርም የማያይ ቢመስልም አይቸኩል እንደ ሰው ይፈርዳል በጊዜው ታማኝ ነው ታማኝ ነው አንዳንዶች እንደዚህ ናቸው መከራው ሲበዛባቸው እምነታቸውን ሲጥሉ አይሰማም አያይም ሲሉ አለ ሁሉንም የሚያይ ከላይ ከሰማይ ( 2x) ስለዚህ አትታበዩ በኩራት አትናገሩ እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል ይፈርዳል ይፈርዳል