አባት አለኝ አባት ሁል ጊዜ የምመካበት ሚረዳኝ ሚራራልኝ ከጐኔ የማይለየኝ ምሕረቱ የበዛ በሕይወቴ ያሳደገኝ ከልጅነቴ እኔ ነኝ እኔ ነኝ እኔ ነኝ ምሕረቱ ያቆመኝ አይተኛም እርሱ እኔን እየጠበቀ ከክፉ አውሬ እየተናጠቀ ያሳድረኛል በለምለሙ ስፍራ በእጆቹ ይዞኛል ክፉን እንዳልፈራ ላምልክህ ወድጄ እጆቼን አንስቼ መልካምነትህ አይተዋል ዓይኖቼ ውሰድ አምልኮዬን መስዋዕቴን ዛሬም አይሰለቸኝ አንተን ማመስገን የወደቀውን ሰው አንስቶ አስውቦ ታሪኩን ለውጦ በምሕረትህ ቆሞ እንደገና ይዞ መጥቷል በዙ ምሥጋና ተመስገን ተመስገን ተመስገን ልበልህ ፡ ባለውለታዬ ክበር እግዚአብሔር አባት አለኝ አባት ሁል ጊዜ የምመካበት ሚረዳኝ ሚራራልኝ ከጐኔ የማይለየኝ ምሕረቱ የበዛ በሕይወቴ ያሳደገኝ ከልጅነቴ እኔ ነኝ እኔ ነኝ እኔ ነኝ ምሕረቱ ያቆመኝ የደከመውን በፍቅር ሚያነሳ ሰው የረሳውን ከቶ የማይረሳ ይቅርታው ብዙ እንደ ሰው አይፈርድ እውነተኛ አባት ልጆቹን ሚወድ ላምልክህ ወድጄ እጆቼን አንስቼ መልካምነትህ አይተዋል ዓይኖቼ ውሰድ አምልኮዬን መስዋዕቴን ዛሬም አይሰለቸኝ አንተን ማመስገን የወደቀውን ሰው አንስቶ አስውቦ ታሪኩን ለውጦ በምሕረትህ ቆሞ እንደገና ይዞ መጥቷል በዙ ምሥጋና ተመስገን ተመስገን ተመስገን ልበልህ ፡ ባለውለታዬ ክበር እግዚአብሔር