Song Lyrics

ቢበራማ

በመንገዴ ስሄድ ስራመድ በሕይወት ጐዳና እግሮቼ በቤትህ ጸንተው ዓይኔ ግን ሳይበራ የሚሄደው የሚመጣው ሲያዳክመው ልቤን የቆምኩኝ ያለሁኝ መስሎኝ እያንገዳገደኝ አልገባኝም ነበር የልቦና ዓይኔ ታውሮ ምድር ምድር አለ የከበረውን ሰማይን ጥሎ ቃልህን ስሰማ ልቤ ተደስቶ ለጊዜው ነበረ በስሜት ተገፍቶ ነፋስና ጐርፉ ሊፈትነኝ መጣ ይታወቀኝ ጀመር ከመንገድ ስወጣ ቢበራማ በቃልህ ቢጸና ዓይኔ ቢበራ ቢበራማ ጸንቶ ይቆም ነበር ፍሬ እያፈራ ቢበራማ ቅርንጫፍ ከግንዱ ከተጣበቀ ቢበራማ ያስታውቃል መልኩ አንተን ያወቀ ዓይኖቼን አብራ ክፈት ዓይኔን እነደ እኔ ሳይሆን እንዳንተ እንዳይ በመንገዴ ስሄድ ስራመድ በሕይወት ጐዳና እግሮቼ በቤትህ ጸንተው ዓይኔ ግን ሳይበራ የሚሄደው የሚመጣው ሲያዳክመው ልቤን የቆምኩኝ ያለሁኝ መስሎኝ እያንገዳገደኝ አልገባኝም ነበር የልቦና ዓይኔ ታውሮ ምድር ምድር አለ የከበረውን ሰማይን ጥሎ ሲዘነጋ ለቤ የሰማዩን ቤቱን በዚህ ምድር ፡ሲኖር እንግዳ መሆኑን አይጐመጅም ነበር ለምድራዊው ኑሮ የሰማዩን ዓለም አንዴ ቢያየው ኖሮ ቢበራማ የተጠራበትን የክብር ተስፋ ቢበራማ የዘላለም እርስት ከቶ ማይጠፋ ቢበራማ ዓይኖቼ ተከፍቶ ይህንን ቢያይ ቢበራማ ይናፍቃል ልቤ ወደ ሰማይ ዓይኖቼን አብራ ክፈት ዓይኔን እነደ እኔ ሳይሆን እንዳንተ እንዳይ ልመናዬ ይሄ ነው አብራው ዓይኔን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection