Song Lyrics

እጄን አነሳሁ

የልቤን ማዋየው የውስጤን ሚስጥረኛዬ ባዝንም ብከፋም ማይለየኝ መጽናኛዬ ነፍሴ ትረካለች በአንደበቱ ቃል በምክሩ የመኖሬ ትርጉም እርሱ ብቻ ነው ሚስጥሩ ወደ አባቴ ልቅረብ እንጂ የሚረዳኝ የለም ከእርሱ ውጪ ወደ አባቴ ልቅረብ እንጂ የሚረዳኝ የለም ከእርሱ ውጪ እጄን አነሳሁ ወደ ላይ ወደ ሚሰማኝ ወደሚያይ ጩኸቴን ሰምቶ ይመልሳል እንባዬን ከዓይኔ ያብሳል አባበዬ አባትዬ አባብዬ ከእስትንፋሴ ይልቅ ይቀርበኛል አይርቀኝም የፍቅር ቃል ኪዳን ገብቶልኛል አይተወኝም እንዳወራው ድፍረት ይሰጠኛል የፍቅር ዓይኖቹ ልቤ ተፈወሰ ሲዳስሰኝ በመልካም እጆቹ መልካም ነህ መልካም መልካም ነህ መልካም ነህ መልካም መልካም ነህ የልቤን ማዋየው የውስጤን ሚስጥረኛዬ ባዝንም ብከፋም ማይለየኝ መጽናኛዬ ነፍሴ ትረካለች በአንደበቱ ቃል በምክሩ የመኖሬ ትርጉም እርሱ ብቻ ነው ሚስጥሩ ወደ አባቴ ልቅረብ እንጂ የሚረዳኝ የለም ከእርሱ ውጪ ወደ አባቴ ልቅረብ እንጂ የሚረዳኝ የለም ከእርሱ ውጪ እጄን አነሳሁ ወደ ላይ ወደ ሚሰማኝ ወደሚያይ ጩኸቴን ሰምቶ ይመልሳል እንባዬን ከዓይኔ ያብሳል አባበዬ አባትዬ አባብዬ ትዋሽ ዘንድ እንደሰው አይደለህ እውነተኛ ነህ የተናገርከውን ታደርጋለህ ትፈጽማለህ ቢታመኑህ ታማኝ አንተ በቻ ወረት የሌለህ ከአጠገቤ ሁሌ ማትለየኝ አንተ ብቻ ነህ መልካም ነህ መልካም መልካም ነህ መልካም ነህ መልካም መልካም ነህ ትልቅነትህ እየገረመኝ አጠገቤ ነህ ይሄም ሲደንቀኝ ዘልቀህ ውስጤ ገብተሃል መኖሪያህን አድርገሃል የእኔ ሆነሃል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection