አምላክ ሰውን ሰራ መልኩን ፈለገና አብሮት እንዲኖር ፍቅር ያዘውና የሰው ልጅ አመፀ ልቡን አደንድኖ አውቆ እንዳልሰማ ጆሮ ዳባ ብሎ የአምላክ ዓላማ ሰውን ሲፈጥር ምድርን ገዝቶ እንዲኖር አትንካ ያለውን ፍሬን ሲበሉ ባለመታዘዝ ከእርሱ ተጣሉ ኢየሩሳሌም ፥ ኢየሩሳሌም ሆይ ፍቅር ግድ አለው ሞቶ ሊያድናት መጥቶ ሊወስዳት አጭቷት ሄደ እንድትዘጋጅ ጊዜ ቢሰጣት ውበቷ ጠፋ ይባስ ተካደ ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ አዝ፦ ኢየሩሳሌም ሆይ (ኢየሩሳሌምሆይ) ኢየሩሳሌም ሆይ ኢየሩሳሌም ሆይ (ኢየሩሳሌምሆይ) የሃይማኖት ቤት አንቺን ለሚያይ ወገኛ ግብዝ ፈሪሳዊ በአንደበትሽ ታከብሪዋለሽ ልብሽ እርቆ አንቺ አስመሳይ ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ አንድ አካል አርጐ ሰርቶሽ ነበረ ጐራ ለይተሽ ፈራርሰሽ የቀድሞ መልክሽ ውበትሽ የለም ተይ ተመለሺ ሳይለይሽ ኢየሩሳሌም ፥ ኢየሩሳሌም ሆይ አዝ፦ ኢየሩሳሌም ሆይ (ኢየሩሳሌምሆይ) ኢየሩሳሌም ሆይ ኢየሩሳሌም ሆይ (ኢየሩሳሌምሆይ) አምላክ አለቀሰ ተረሳሁኝ ብሎ ጅራፉን አነሳ ቤቱ ተመሳቅሎ መች እንዲህ አበጀሽ ተለውጧል መልክሽ ቀናተኛ ነው ጌታ ሌላ ያሰኘሽ ለታ እወድሽ የለም ወይ ሙሽራዬ ሆይ ተውበሽ ጠብቂኝ መጽዳትሽን ልይ መጥቼ እንደወስድሽ ወደኔ ተመለሺ እኔ ቅዱስ ነኝና ተነሽ ደሜን እዪና የት ነው ያለሽው (ሙሽራይቱ) ናፍቆሻል እርሱ (ሙሽራይቱ) በይ ተዘጋጂ (ሙሽራይቱ) ደርሷል ሰዓቱ (ሙሽራይቱ) ነቅተሽ ጠብቂው (ሙሽራይቱ) በንጹህ ሕይወት (ሙሽራይቱ) የአንቺ ትጉነት (ሙሽራይቱ) የእርሱ ፍጥነት (ሙሽራይቱ) ምፅአቱ ቀርቧልና (4x)