Song Lyrics

ፈቶኛልና

Yosef Kassa
Teneshina Abiri
በባርነት በቀምበር ተይዞ የተስፋው ሕዝብ በሃዘን ተውጦ የሰቆቃ ጩኸቱን ሰማና አሳረው ታደገውና አቤት የእርሱ ሥራ ነፃነቴን ቃሉ ነገረኝ እኔን እመን ቀና በል አለኝ ተፈትተሃል ምንድነው ጭንቀት መጠራትህ ለነፃነት አቤት የእርሱ ሥራ ከላይ ወረደ ሕዝቡን ሊያሳርፍ በመስቀል ላይ ሞቶ (ከላይ ወረደ ሕዝቡን ሊያሳርፍ በመስቀል ላይ ሞቶ) የታሰሩትን ነፃ ሊያወጣ መፈታትን ይዞ (የታሰሩትን ነፃ ሊያወጣ መፈታትን ይዞ) ቀንበር ተሰብሯል አይዞህ አትፍራ ተረጋግተህ ኑር (ቀንበርተሰብሯል አይዞህ አትፍራ ተረጋግተህ ኑር) ተከፍቷል በሩ አምነህ ተራመድ አለኝ እግዚአብሔር (ተከፍቷልበሩ አምነህ ተራመድ አለኝ እግዚአብሔር) (ፈቶኛልና) የኋላዬን አላይ (ፈቶኛልና) የፊት የፊቴን እንጂ (ፈቶኛልና) አዕምሮዬ ታድሷል (ፈቶኛልና) ነፃነቴንላውጅ (ፈቶኛልና) በፊቱ እዘላለሁ (ፈቶኛልና) እንደተፈታ ሰው (ፈቶኛልና) ጠላቴም ይፈር ይፈር (ፈቶኛልና) የፈታኝ ኢየሱስ ነው (ነፃ ላወጣን ለጌታ) ምሥጋና (ነፃ ላወጣን ለጌታ) እልልታ (ነፃ ላወጣን ለጌታ) ዘምሩ (ነፃ ላወጣን ለጌታ) እልል በሉ . (1) . (ነፃ) ከሀጥያት (ነፃ) ከእስራት (ነፃ) ከፍርሃት (ነፃ) ነፃ ነኝ (2x) ይኸው እልልታ (8x) የፈታኝ ነገረኝ ቀሰቀሰኝና ቀንበርህ ተሰብሯል በል ሂድ ተነሳና ተፈቶ ዝም የለም ይሰማል ምሥጋና የዘመናት ታሪክ ተለውጧልና ለፈታኝ (እኔ አለኝ ምሥጋና) ላዳነኝ (እኔ አለኝ ምሥጋና) ለጌታ (እኔ አለኝ ምሥጋና) ለኢየሱሴ (እኔ አለኝ ምሥጋና) (2x) ይኸው እልልታ (8x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection