ቃልህን ሰምቼ ተጽናናሁኝና ይፈጸማል ብዬ ነገን ጠበቅኩና ጊዜው ሲገፋ አስጨነቀኝ ያልከኝም ምንም አልሆነልኝ ይልቁን መከራ ሆነብኝ ምንድነው ጉዱ መላ በሉኝ ወተትና ማርን የምታፈስ ሀገር አወርሳችኋለሁ ብለህ ለእስራኤል [1] መንገድ ሲጀምሩ መከራቸው በዛ የተናገርካቸው ሁሉ እስኪረሳ [2] ያልከው ግን ሌላ የሚሆነው ሌላ (2x) መች በረሃ ቀሩ ቃሉ ተፈፀመ አትዘገይም አንተ ያልከው ሁሉ ሆነ [3] ምንም ብትዘገይም ትመጣለህና እጠብቅሃለሁ የእኔም ቀን አለና ያልከው ግን ሌላ የሚሆነው ሌላ (2x) አንተ ያልከኝ ሌላ ነው የሚሆንብኝ ሌላ ነው ምንድነው ነገሩ ወዴት ነው ሚስጥሩ አስተምረኝ አዝ፦ (ጊዜ አለው ለሁሉም) ኧረ ነፍሴ ረጋ በዪልኝ (ጊዜ አለው ለሁሉም) ያደርገዋል እርሱ ካለኝ (ጊዜ አለው ለሁሉም) ሳይፈፀም ጊዜው ቢገፋም (ጊዜ አለው ለሁሉም) እጠብቃለሁ የትም አልሄድም (2x) ዮሴፍ ወንድሞቹ ሲሰግዱለትአየ እንደምታከብረው እንዲነግስ አለመ [4] ነገር ግን ሲነሳ ሊገድሉት ተነሱ በግዞት ተጣለ ህልሞቹም ተረሱ [5] ያልከው ግን ሌላ የሚሆነው ሌላ (2x) ዘመናት ቢፈጅም ህልሙ ተፈጸመ የማይሆን ቢመስልም እንዳየው ግን ሆነ በለሱን የሚጠብቅ ፍሬዋን ሊበላ ለታገሱ ሁሉ ጊዜ አለህና ያልከው ግን ሌላ የሚሆነው ሌላ (2x) አንተ ያልከኝ ሌላ ነው የሚሆንብኝ ሌላ ነው ምንድነው ነገሩ ወዴት ነው ሚስጥሩ አስተምረኝ አዝ፦ (ጊዜ አለው ለሁሉም) ኧረ ነፍሴ ረጋ በይልኝ (ጊዜ አለው ለሁሉም) ያደርገዋል እርሱ ካለኝ (ጊዜ አለው ለሁሉም) ሳይፈፀም ጊዜው ቢገፋም (ጊዜ አለው ለሁሉም) እጠብቃለሁ የትም አልሄድም (2x) አምላኬ ጊዜው ሲሄድብኝ መላ ፍለጋ አጋር ቤት ገብቼ እንዳልጐዳ አስተዋይ አርገኝ ትዕግስትን ስጠኝ (2x) ጌታዬ አንተን ተስፋ አድርጌ አላፍርምና በራስህ ጊዜ ይሆናልና እባክህ እርዳኝ ታጋሽ አርገኝ (2x)