Song Lyrics

መኖር አልችልም

Yosef Kassa
Teneshina Abiri
ሁልጊዜ ምናፍቅህ የነፍሴ ጥማት የምትወድህ ልዑል ነህ ለእኔ እርሱ ነው ረሃቤ ያለ አንተ መኖር አልችልም ታውቃለህ አቅም እኔ የለኝም ኢየሱሴ የእኔ አትሂድብኝ ከእኔ አዝ፦ አትሂድብኝ ደካማ ነኝ ያለ አንተማ አቅም የለኝም (2x) ባጠፋም ልጅህ ነኝ ቅጣኝ ግን መንፈስህ እንዳይርቀኝ የሕይወት እስትንፋሴ ህልውናህ ነው ኢየሱሴ ስትርቀኝ ይከፋኛል አንተን መፍራት ይከብደኛል የምትረዳኝ ረድኤቴ አትሂድ ከሕይወቴ አዝ፦ አትሂድብኝ ደካማ ነኝ ያለ አንተማ አቅም የለኝም ዝናህ ሀብት ሞልቶ ጐተራዬም ቢሞላም አዬ መኖር አልችልም እኔ ስትለየኝ ከጐኔ (2x) መኖር ይከብደኛል ሕይወትም ይታክተኛል መኖር አልችልም እኔ ስትለየኝ ከጎኔ (2x) አባብዬ የእኔ ጌታ ናፍቆቴ ነህ ጠዋትም ማታ ህልውናህ መገኘት ደስታን አጠገበኝ ፊትህ (2x) ፊትህን ሳየው ውስጤን ደስታ ትሞላኛለህ ምንም ባይኖረኝ ምንም አንተው ትበቃኛለህ (2x) መኖር አልችልም እኔ ስትለየኝ ከጐኔ መኖር አልችልም እኔ ስትለየኝ ከጐኔ (5x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection