Song Lyrics

ጌታ ከኛ ጋር

Yosef Kassa
Teneshina Abiri
ሊወጋኝ ጠላት ከቦኝ ፥ ሲፎክር ሲያስፈራራኝ አምላኬን ስመለከት ፥ ልቤ ተሞላ በእምነት የልብ ዓይኖቼን ሲያበራ ፥ አየሁ የእሳት ሰረገላ በል ግጠማቸው ውጣና ፥ አስቀድምልኝ ምሥጋና አዝ፦ ጌታ (ከእኛ ጋር) በመንፈሱ (ከእኛ ጋር) ኢየሱስ (ከእኛ ጋር) በመንፈሱ (ከእኛ ጋር) ሰልፉ ሲበዛ ፈራሁኝ ብዬ አምላኬን ጠየቅኩ ምን ላድርግ ብዬ ልጄ ምሥጋና ጀምር አለኝ በድብቅ ጦሩ ሊፈጅልኝ ጠላት ወደቀ (ምሥጋናን ይዤ) ተንኮታኮተ (ምሥጋናን ይዤ) ቃሉን ለብሼ (ምሥጋናን ይዤ) ሰይፌን ይዤ (ምሥጋናን ይዤ) አትደናገጥ በምትሰማው በሟርት በዛቻቸው ከአንተ ጋር ያለው ይበልጣልና ታድያ ሳቅባቸው ቀድሞም ጠላትህ ወድቋልና በእምነት ጀምር ምሥጋና አዝ፦ ጌታ (ከእኛ ጋር) በመንፈሱ (ከእኛጋር) ኢየሱስ (ከእኛ ጋር) በመንፈሱ (ከእኛጋር) ጠላቱ የተቀጣ (ጠላቱ የተቀጣ) ለአምላኩ ክብር ያምጣ (ለአምላኩ ክብር ያምጣ) ይደርደር በገናው (ይደርደር በገናው) ይመታ ከበሮው (ይመታ ከበሮው ) ምሥጋና (ለእርሱ) እልልታ (ለእርሱ) ምሥጋና (ለእርሱ) እልልታ (ለእርሱ) ምሥጋና (ለእርሱ) እልልታ (ለእርሱ) (2x) (ጋሞኛ) አላጋይ ኩንዶ አሲ ፨ጠላቱ የወደቀለት ሰው፨ አን ቃማይ ዎንቶ አሲ ፨በእርሱ ምሽቱ የነጋለት ሰው፨ ማሲንቂያ ካራቢያን ፨ማሲንቆ ከከበሮ ጋር፨ አባዋራ ባናው ቤሴስ ፨በጣም ሊያሰማው ይገባል፨ ጋላታይ(አሳ) ፨ምስጋና (ለእርሱ) ቦንቾይ(አሳ) ፨ክብር (ለእርሱ ) እልልሳይ(አሳ) ፨እልልታ (ለእርሱ ) ጎይኖይ(አሳ) ፨አምልኮ (ለእርሱ ) 1(ሀኢ ኑናራ ዴኔ ጾሳይ) ዎሲን ሲያናው 2(ሀኢ ኑናራ ዴኔ ጾሳይ) ጼሲን ኮያናው 3(ሀኢ ኑናራ ዴኔ ጾሳይ) ሜትን ማዳናው 4(ሀኢ ኑናራ ዴኔ ጾሳይ) 1 (አሁን ከእኛጋር አለ እግዚአብሔር` ) ጸሎት ሊሰማ 2 (አሁን ከእኛጋር አለ እግዚአብሔር` ) ስንጣራው ሊመልስን 3 (አሁን ከእኛጋ አለ እግዚአብሔር ) ሲቸግረን ሊረዳን 4 (አሁን ከእኛጋ አለ እግዚአብሔር አሳ[×]
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection