Song Lyrics

አያለሁ

Yosef Kassa
Nuroye Bekidan New
የውስጤ የእኔ ፍላጐቴ ክብርህ ነው የሁሌ ጥማቴ ለሃገር ለወገን መፍትሄ ስንሆን የተወሰድብን ሲመለስልን ይሄ ነው ጥማቴ የውስጤ ርሃቤ ይህንን አያለሁ አምኖሃል ልቤ የቤትህ ስርአት ተበላሽቶ ተው የሚል የሚመልሰን ጠፍቶ ይህ ሁሉ አካሄድ ያቆምና አያለሁ ታድሶ እንደገና አዝ፦ አያለሁ ክብርህ ቤትህን ሞልቶ አያለሁ ያዘነው ተጽናንቶ አያለሁ የፈረሰው ቅጥር አያለሁ ታድሶ በክብር አያለሁ ሰው ሁሉ ሲገረም አያለሁ ትንቢቱም ሲፈጸም ከጥንቱ የነበረው ሃይልህ ለትውልድ መፍትሄ የነበርህ አያለሁ የአንተ ክብር ሲያበራ በእጥፍ በዚህ ዘመን ሲሰራ አዝ፦ አያለሁ ክብርህ ቤትህን ሞልቶ አያለሁ ያዘነው ተጽናንቶ አያለሁ የፈረሰው ቅጥር አያለሁ ታድሶ በክብር አያለሁ ሰው ሁሉ ሲገረም አያለሁ ትንቢቱም ሲፈጸም ሕይወቱ ኑሮው የጨላለመ በሃዘን ልቡ የደካከመ አያለሁ የአንተ ክብር ሲመጣ ጥያቄ ነገር ሁሉ ሲፈታ አዝ፦ አያለሁ ክብርህ ቤትህን ሞልቶ አያለሁ ያዘነው ተጽናንቶ አያለሁ የፈረሰው ቅጥር አያለሁ ታድሶ በክብር አያለሁ ሰው ሁሉ ሲገረም አያለሁ ትንቢቱም ሲፈጸም
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection