አዝ፦ የወደደህ ልቤ በእኔ ማንነቴ ድንቅ ድንቅ አየሁኝ በአንተ ሁሌ በሕይወቴ በአንተ ተይዣለሁ ማነው የሚወስደኝ ፍቅርህ እኔን ስቦኛል አልሰጋም ተመችተኽኛል (2x) አቤቱ ከልቤ ላመስግንህ አንተን ምሥጋናን ዝማሬ ማታ ቢሆን በቀን እሰዋልሃለሁ የእውነቴን ሆኜ ከአንተ ወዲያ ፍቅር አላየሁም እኔ (2x) ለእኔ ሚሆነኝ ከአንተ ወዲያ የለኝም አንተ ነህ የእኔ መመኪያ በአንተ ሕይወትን እኔ አግኝቻለሁ ኢየሱስ ለአንተ እዘምራለሁ ያለምንም እኔን የወደደ ፍቅር እንደ ጌታ የት አለ ለሰው የሚያዝን የሚራራ ኧረ እንደኢየሱስ የለም ሌላ ታዲያ ለኢየሱስ ቢዘመር የእርሱ ታላቅነት ቢነገር እርሱ ከወደደው ይሄ ሁሉ እዘምራለሁኝ በየቀኑ አዝ፦ የወደደህ ልቤ በእኔ ማንነቴ ድንቅ ድንቅ አየሁኝ በአንተ ሁሌ በሕይወቴ በአንተ ተይዣለሁ ማነው የሚወስደኝ ፍቅርህ እኔን ስቦኛል አልሰጋም ተመችተኽኛል (2x) አቤቱ ከልቤ ላመስግንህ አንተን ምሥጋናን ዝማሬ ማታ ቢሆን በቀን እሰዋልሃለሁ የእውነቴን ሆኜ ከአንተ ወዲያ ፍቅር አላየሁም እኔ (2x) የእውነት የማይጠፋ ፍቅር ያለህ እንደአንተ እንደጌታዬ የት አለ እንደሰው የማትለዋወጥብኝ አንተ ነህ ከጐኔ ለእኔ ያለኽኝ ያለምንም እኔን የወደደ ፍቅር እንደ ጌታ የት አለ ለሰው የሚያዝን የሚራራ ኧረ እንደኢየሱስ የለም ሌላ ታዲያ ለኢየሱስ ቢዘመር የእርሱ ታላቅነት ቢነገር እርሱ ከወደደው ይሄ ሁሉ እዘምራለሁኝ በየቀኑ (2x)