Song Lyrics

እግዚአብሔር ይነሳል

Yosef Kassa
Nuroye Bekidan New
እግዚአብሔር ይነሳል ክብሩን ይመልሳል እኔ እምቢ ብል እንኳን ትውልድን ያስነሳል ጌታዬ ይነሳል ክብሩን ይመልሳል እኔ እምቢ እንኳን ያናውን ያስነሳል ፍቅር ተለማምዶ ምህረት የሚያወራ አንተን አሳዝኖ ምንም የማይፈራ ሲታይ መልአክ ነው ውስጡ የፈረሰ ሊታደስ ይችላል ሃይልህ ከፈሰሰ አዝ፦ አንዴ ጠብቀን እድልን ስጠን እንመለሳለን እጅህ ሳትመታን አንዱ ከአንዱ ጋራ የታለ ፍቅር መያያዙን ትቶ ወሬ ሲቆፍር አንድነት የለውም ተነካክሶ አለቀ ይሄ ክፉ መዘዝ ለሌላም ዘለቀ አዝ፦ አንዴ ጠብቀን እድልን ስጠን እንመለሳለን እጅህ ሳትመታን መለክት አለኝ ብሎ ከቃልህ የወጣ ከአንተ አስመስሎ ከራሱ ያመጣ በስሜት ተገፍቶ ህዝቡን እያመሰ በዚህ ነገር እንኳን ስንቱ አለቀሰ አዝ፦ አንዴ ጠብቀን እድልን ስጠን እንመለሳለን እጅህ ሳትመታን በዕውቀት ተወጥሮ መስሎት የአደገ ለስተቱ ሁሉ ጥቅስ እየፈለገ ያለ እየመሰለው ጠፋ ይሄ ስዉ ማወቅ መች ጠቀመው ሕይወት ከሌለው አዝ፦ አንዴ ጠብቀን እድልን ስጠን እንመለሳለን እጅህ ሳትመታን እግዚአብሔር ይነሳል ክብሩን ይመልሳል እኔ እምቢ ብል እንኳን ትውልድን ያስነሳል ይሄ ለጥቅሙ ያኛውን ሲገፋ ራሱን ለማሳየት መለከት ሲያስነፋ የአንተን ተወት አድርጐ ለእራሱ ሲጥር ክብርህን ተጋፍተውን ጠፍተን እንዳንቀር ሕይወትን ሰጥተኸው ከእጅህ ላይ በልቶ እንዴት ነው ሚለየው ሄዶ ተቀይጦ ስምህን ግን ይዟል ተግባሩ ግን ሌላ እየተዘናጋን ጽዋህ እንዳትሞላ አዝ፦ አንዴ ጠብቀን እድልን ስጠን እንመለሳለን እጅህ ሳትመታን እስቲ ጠብቀን ትንሽ ታገሰን እንመለሳለን ሳታዋርደን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection