ሰማዩ ጸጥ አለ ያ ዝናቡ ጠፋ ዳመናም አይታይ ምንም አያካፋ ምድርም ጸጥ አለች መሬቱም ደረቀች ለምልሞ የነበረው ጠውልጐ አለቀ ሰው ገሸሽ አለ ከቀኝ ከግራዬ ተስፋ ቢስ አደረጉኝ በዝቶ መከራዬ አሁን ተሳሳቱ መች እንዲህ ልቀር በጊዜው ይመጣል ተስፋ የእግዚአብሔር አዝ፦ ሰማይ ጸጥ ቢል ዝናብ ባይዘንብ ምድርም ደርቃ ብትጠወልግ (አምንሃለሁ) ደማናም ሳይኖር ዝናብ ይዘንባል ባዶ ሸለቆ ውኃ ይሞላል (አምንሃለሁ) ዘመድ አዝማዴ ከእኔ ቢርቅ ንብረቴ ያልኩት ተወስዶ ቢያልቅ (አምንሃለሁ) አንተ እግዚአብሔር የፍጥረት ጌታ ፈጥነህ የምትደርስ ያመኑህ ለታ (አምንሃለሁ) አብርሃም አረጀ ሳራም ያው ደከመች ዕድሜያቸው አበቃ ልጅ የሚስሙበት የአብራሃም መድከው ጌታን መች ቸገረው ያዛሬ አመት ልጅን ትወልዳለህ አለው ኧረ እንዴት ይሆናል ብለው ተሳሳቁ የማይሆን መስሏቸው ያለውን ሳያውቁ በእርግጥም ይመስላልከሚታየው ነገር አንተ እመን እንጂ ቀላል ነው ለእግዚአብሔር አዝ፦ ነገሬ ቢቆይ ቢዘገይ እንኳን የምፈልገው አሁን ባይመጣም (አምንሃለሁ) የማየው ነገር ግራ ቢያጋባኝ ያልከውን እንጂ አልሰማም ሌላ (አምንሃለሁ) እንደሰው መቼ ቃልህ ይዞራል ለሚያምኑህ ሁሉ መልካም ሆነሃል (አምንሃለሁ) አንተ ተናግረህ ማይሆን ምን አለ ሁሉን በጊዜው ውብ ታደርጋለህ (አምንሃለሁ) ጻድቅ ሰው ነበር እዮብ የተባለ እጅግ ባለፀጋ የተደላደለ ግን ድንገት ያሃብቱ ንብረቱ ወደቀ ሰይታን ሊፈትነው በብዙ ደከመ ሚስቱም እግዚአብሔርን ሰድበህ ሙት አለችው የነበራት ሁሉ ጠፍቶ ስላየቺው አንቺ ሰነፍ ብሎ ተቆጣ ይህ ጀግና እግዚአብሔር አምኖ ሊሞት ወሰነና ግን መቼ እንደዚህ ሕይወቱ አለፈ በፊት ከነበረው አምሮበት አረፈ አዝ፦ ሃብቴ ንብረቴ ከእኔ ነበረ ድንገት ከእጄ ሁሉም በረረ (አምንሃለሁ) ምንም ባይኖረኝ አንተን ይዣለሁ መከራዎቼን በአንተ አልፋለሁ (አምንሃለሁ) ይህ ሰውነቴ ቢዝል ቢደክም በሽታ በእኔ ቢፈራረቅም (አምንሃለሁ) አንተ እግዚአብሔር የእኔ አባት አንተን አምኜስ ልሞት (አምንሃለሁ) እመን ወንድሜ ታመን በእግዚአብሔር አትሞኝ ጌታን አትገምተው በቀላል ነገረ እመኜ እህቴ ታመኜ በእግዚአብሔር አትሞኝ ጌታን አትገምቼው በቀላል ነገረ እመን ወገኔ ታመን በእግዚአብሔር አትሞኝ ጌታን አትጠርጥረው በቀላል ነገር እመን ልቤ ሰማይ ምድሩ እመን ልቤ የፈጠረው እመን ልቤ የተናገረው እመን ልቤ የሚያደርገው እመን ልቤ ተስፋ ቢዘገይ እመን ልቤ ባይነጋም ሌቱ እመን ልቤ አስታውስ አንጂ እመን ልቤ አምነው የሞቱ እመን ልቤ መቼ ከሰሩ እመን ልቤ በእርሱ የታመኑ እመን ልቤ በእምነታቸው እመን ልቤ ድልን አገኙ