Song Lyrics

ፍቅር ነህ

Yosef Kassa
Nuroye Bekidan New
ብዙ አሉ በምድር ፍቅር አለን ሚሉ የወደደውን ሚወድ ሞልቷል በሃገሩ መች እንደዚህ ሆነና የአንተ ፍቅር ከሰው ይለያል የአንተ የእግዚአብሔር (2x) ጠፍቼ ነበረ ያኔ በዚያን ጊዜ ሙት ሆኜ ማልረባ ከአንተ ተለይቼ እንዲሁ አልተውከኝም በፍቅርህ አዳንከኝ በምትወደው ልጅህ በኢየሱስ ታረቅከኝ ምን ብዬ እኔስ ልናገር ስለአንተ ፍቅር ጠፍቼ እንኳን ምትፈልገኝ መክረህ የምትመልሰኝ ፍቅር ነህ ሁሌ የማትለወጥ ፍቅር ነህ ፍቅር ነህ አንተ ዛሬም (2x) መልካም ነህ አንተን ዛሬም (2x) በእምነቱ ደክሞ በሰው የተገፋ ሚያንገላታው እንጂ ሚያነሳው የጠፋ የቅን ፈራጅ አንተ በፍቅርህ ፈርደህ አንስተህ ለወጥከው አንተ ልክ ነህ ፍቅር ነህ አንተ ዛሬም (2x) መልካም ነህ አንተን ዛሬም (2x) ልዩ ነህ አንተ ዛሬም (2x) ወዳጅ ነህ አንተ ዛሬም (2x) አንተ ዛሬም (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection