ያን ያረክልኝ የማልረሳው ለእኔ ብለህ ነው ሞቴን የሞትከው ለሕይወቴ ቤዛ ባትሆን ኖሮ የት እገኝ ነበረ ያኔ ድሮ (አዬ ያኔ ድሮ) ሁሌ ይህን ሳስብ የሚደንቀኝ በመስቀል ላይ ለእኔ ያዋልክልኝ ያኔ በሰራኸው ታላቅ ስራ ሕይወትን አገኘሁ እንደገና (አዬ እንደገና) አዝ፦ ለዚህ ነው ሁሌ ምዘምረው ሁሌ ከእኔ ጋር ያለ እንደ አንተ ሰለሌለ ገና ከዚህም በላይ አመልካለሁ ሁሌ ከእኔ ጋር ያለ እንደ አንተ ሰለሌለ እኔስ ደስ አለኝ የአንተ በመሆኔ ሁሌ ከእኔ ጋር ያለ እንደ አንተ ሰለሌለ ከምንም በላይ ልዩ ነህ ለእኔ ሁሌ ከእኔ ጋር ያለ እንደ አንተ ሰለሌለ ከአንተ ጋራ ሆኖ ማነው የከሰረ አንተን ተጠግቶ ኧረ ማን አፈረ ለቀረቡት ሁሉ መልካም የሚያደርግ እስቲ እንደኢየሱስ ኧረ ማነው ደግ (2x) እናት እንኳን ልጇን ብትረሳው የነበራት መውደዷ ቢረሳት አንተ አትለወጥ እንደሰዉ የአንተ የዘለዓለም ፍቅር ነዉ (አዬ ፍቅር ነው) ሁልጊዜ አንተ ከእኔ ጋራ ታበረታኛለህ እንዳልፈራ ከእናት አባት በላይ የሆንከኝ በአንተ ተደግፌ አረፍኩኝ (አዬ አረፍኩኝ) አዝ፦ ለዚህ ነው ሁሌ ምዘምረው ሁሌ ከእኔ ጋር ያለ እንደ አንተ ሰለሌለ ገና ከዚህም በላይ አመልካለሁ ሁሌ ከእኔ ጋር ያለ እንደ አንተ ሰለሌለ እኔስ ደስ አለኝ የአንተ በመሆኔ ሁሌ ከእኔ ጋር ያለ እንደ አንተ ሰለሌለ ከምንም በላይ ልዩ ነህ ለእኔ ሁሌ ከእኔ ጋር ያለ እንደ አንተ ሰለሌለ ከአንተ ጋራ ሆኖ ማነው የከሰረ አንተን ተጠግቶ ኧረ ማን አፈረ ለቀረቡት ሁሉ መልካም የሚያደርግ እስቲ እንደኢየሱስ ኧረ ማነው ደግ (2x) ልክ እንደ ጌታዬ ኧረ ማነው ደግ ሕይወቱን የሰጠኝ ኧረ ማነው ደግ ወድሃለሁ ብሎ ኧረ ማነው ደግ ልጁ ያደረገኝ ኧረ ማነው ደግ (3x)