Song Lyrics

ይሄውና ልቤ

Yosef Kassa
Nuroye Bekidan New
ልቤን ይኽው እያት ወደ አንተ መልሳት ልቤን ይኸው እያት እንደ አንተ አድርጋት በሰው ልብ ብዙ ሃሳብ ምኞት ይገኛል ዘወትር ከራሱ ጋር ሁሌ ያወራል አንደኛው ስለምድር ሁሌ ያስባል ያ ደግሞ ሰማያዊውን ይናፍቃል ይህ ልቤ የሚመኘው አንተን ካልሆነ መኖሩ ትርጉም የለው ያው ከንቱ ሆነ (ይሄውና ልቤ) በአንተ ይሞላ አንተን ይናፍቅ አንተን ይጠማ (ይሄውና ልቤ) የእኔ አትሁን የአንተ አድርጋት ውሰዳትና (ይሄውና ልቤ) እባክህ ልጄ ልብህን ስጠኝ ብለሃልና (ይሄውና ልቤ) እስቲ ልወጣት የአንተን ዐይነት ??? አድርገህ ቃኛት (ይሄውና ልቤ) ዘምሮ አጨብጭቦ ዘሎ ይወጣና ያለቅሳል እንደገና ቤቱ ይገባና በምድር ብዙ አሉ ልብ የሚጐዱ መሽገው በጨለማ የሚናደፉ ጠብቃት እቺ ልቤ እንዳትጐዳ አበርታኝ ልቤ ሁልጊዜ በአንተ ትጽና (ይሄውና ልቤ) በምድር አሉ ከጐኔ ሆነው ልብ የሚገድሉ (ይሄውና ልቤ) ሊያሳዝኗት ልቤን ለመጣል የሚማማሉ (ይሄውና ልቤ) እኔ ከያዝኳት በትንሽ ነገር ትሸነፋለች (ይሄውና ልቤ) አንተ ከያዝካት ሁልጊዜ ደስታ ሁሌ ብርቱ ናት (ይሄውና ልቤ) ልቤን ይኽው እያት ወደ አንተ መልሳት ልቤን ይኸው እያት እንደ አንተ አድርጋት አምላኬ ጌታዬ ነህ ገዢዬ ብዬ ግን ሌላ ነገር በልቤ ላይ አዝዬ ወንድሜን አብሮኝ ያለውን እየጠላ ቂም ይዞ ሲጸልይ ሲዘምር አይፈራ ይህ ልቤ ይቅርታን ማድረግ ካላወቀ ከአንተ የሚያገኘው ምህረት አለቀ (ይሄውና ልቤ) ማይገባውን አስቀመጠና ይሄው ተበላሸ (ይሄውና ልቤ) በሰው እያዘነ ውስጡን ውስጡን ግን ልቤ ቆሸሸ (ይሄውና ልቤ) እስቲ ለውጠው ይህ ካልሆነ እጐዳለሁና (ይሄውና ልቤ) ንጹህ ልብ ስጠኝ አንተን ለማየት አልችልምና (ይሄውና ልቤ) ወጣሁኝ ተሳካልኝ ሆነልኝ ብዬ ሌት ተቀን ሳመሰግን በዝቶ ደስታዬ የእኔን መውደቅና ሃዘን የሚመኝ ይመጣል ከወጣሁበት ሊያወርደኝ ይህ ልቤ አንተን አምኖ ካልጠነከረ ይረታል መጨረሻው ያው ተሰበረ (ይሄውና ልቤ) የእኔን መሳካት መከናወኔን ክፉ ሲሰማ (ይሄውና ልቤ) ብዙ ይተጋል ከአንተ ሊለየኝ ልቤን ሊያደማ (ይሄውና ልቤ) ካልጠነከረ የአንተ ለመሆን ካላመረረ (ይሄውና ልቤ) ቶሎ ይረታል በአንተ ፍቅር ካልተቃጠለ (ይሄውና ልቤ) አንዳንዴ ይሄ ልቤ ይጠራጠራል ስትዘገይ የማትሰማውም ይመስለዋል ነገሮች ብዙ በላዩ ሲከብዱበት ሲያዝን የተናገርከው ሲጠፉበት ለሚያልፍ ከእኔ ጋራ ለማይቆየዉ ሲሸነፍ ይሄውልህ ጌታ እየዉ (ይሄውና ልቤ) በፍፁም ልብህ ታመን ያልከው እረሳሁና (ይሄውና ልቤ) ተጠራጠረ የማያልፍ መስሎት ደነበረና (ይሄውና ልቤ) ኧረ ፈውሰው ከሃሳብህ ጋር እስኪ አስማማው (ይሄውና ልቤ) ይኸው ለውጠው ልብህን ክልቤ እጠበው (ይሄውና ልቤ) ልቤን ይኽው እያት ወደ አንተ መልሳት ልቤን ይኸው እያት እንደ አንተ አድርጋት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection