Song Lyrics

ኑሮዬ በኪዳን ነው

Yosef Kassa
Nuroye Bekidan New
ሃገር ምድር ሲናወጥ ሰው ሁሉ ሲታገል ለማምለጥ እየባሰ ግር ግሩ ሕይወቴን ሊረብሽ ሊያስፈሩ ለካ ቆሜ ሳስበው ኑሮዬ በኪዳን ነው ኧረ ከእኔ ጋራ ያለው እርሱ እግዚአብሔር ነው አዝ፦ ኪዳን አለኝ የእውነትም ቃል አለኝ ኢየሱስ ነው ልጁ ያደረገኝ መመኪያዬ የእውነትም ተስፋዬ እርሱ ላይ ነው መደገፊያዬ (2x) እንድጠፋ ፈልጐ ያ ክፉ ሊወጠኝ ሲጥር አልገባውም መሰለኝ እንዳለኝ ሃይለእኛ ቅጥር ሕይወቴን ሊተናኮል ጠጋ ጠጋ ሲለኝ ኪዳኑን የሚያከብረው እግዚአብሔር ወጣልኝ እስኪ በል ተናገር አልኝ እንዴት ነው ሚረዳህ አሉኝ ልናገር አፌን ሞልቼ የመጣውን ከአባቶቼ ያኔም አሁንም ይሰራል አልፎም ያድነኛል የተጽፈውን ሳምን የቃልኪዳኑን (2x) አዝ፦ ኪዳን አለኝ የእውነትም ቃል አለኝ ኢየሱስ ነው ልጁ ያደረገኝ መመኪያዬ የእውነትም ተስፋዬ እርሱ ላይ ነው መደገፊያዬ በሕይወቴ ስፈራ ነገ ስለሚሆነው ሳላቅ ነገ ስለሚሆነው አለኝ ተው አትጨነቅ በነጽነት እንድትኖር ከአንተ ጋራ ነኝ አለኝ ይሄ የእውነት ኪዳን እንዳልሰጋ አረገኝ አዝ፦ ኪዳን አለኝ የእውነትም ቃል አለኝ ኢየሱስ ነው ልጁ ያደረገኝ መመኪያዬ የእውነትም ተስፋዬ እርሱ ላይ ነው መደገፊያዬ እስኪ በል ተናገር አልኝ እንዴት ነው ሚረዳህ አሉኝ ልናገር አፌን ሞልቼ የመጣውን ከአባቶቼ ያኔም አሁንም ይሰራል አልፎም ያድነኛል የተጽፈውን ሳምን የቃልኪዳኑን (2x) አለኝ ቃልኪዳን ከእርሱ ጋራ አለኝ ቃልኪዳን እንዴት ልፈራ (8x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection