Song Lyrics

የለህም እኩያ

Yosef Bekele
Sintun Lawura
ሊታይ በማይቻል ብርሃን ውስጥ አለህ ከምድር ጫፍ እስከጫፍ ሁሉ እኮ ግዛትህ አለቅነት ስልጣን ክብር የአንተ ብቻ እናመልክሃለን ኢየሱስ የለህ ብቻ (2x) አዝ፦ ሃሌሉያ (2x) ሃሌሉያ የለህም እኩያ (2x) የለህም እኩያ (4x) ስግደትና አምልኮ ለጌታ ለሰራዊት ሁሉ አለቃ ለሆንከው አባታችን ንጉሣችን (ንጉሣችን) ፈዋሻችን ነህ አዳኛችን ምርኩዛችን መታመኛችን እርስታችን እግዚአብሔር ሃገራችን (ሃገራችን) እንገዛልሃለን ወድቀን አዲስ ቅኔን እየተቀኘን ክበር ለዘለዓለም ንገሥ ለዘለዓለም ቅዱስ አባታችን ሰማይ ዙፋንህ ነው ምድር መረገጫህ ጊዜና ሁኔታ ቦታ አይወስንህ አሰራርህ ግሩም ከአይምሮ በላይ ነው አገዛዝህ ምቹ ከማንም ልዩ ነው (2x) አዝ፦ ሃሌሉያ (2x) ሃሌሉያ የለህም እኩያ (2x) የለህም እኩያ (4x) ስግደትና አምልኮ ለጌታ ለሰራዊት ሁሉ አለቃ ለሆንከው አባታችን ንጉሣችን (ንጉሣችን) ፈዋሻችን ነህ አዳኛችን ምርኩዛችን መታመኛችን እርስታችን እግዚአብሔር ሃገራችን (ሃገራችን) እንገዛልሃለን ወድቀን አዲስ ቅኔን እየተቀኘን ክበር ለዘለዓለም ንገሥ ለዘለዓለም ቅዱስ አባታችን የጥበብ ሁሉ ምንጭ የዕውቀት መሰረት የሰላም የደስታ የፍቅር ተምሳሌት አንተ እኮ ነህ ጌታ ለእኛስ ማረፊያችን እውነተኛ ወዳጅ ብሩኩ ተስፋችን (2x) አዝ፦ ሃሌሉያ (2x) ሃሌሉያ የለህም እኩያ (2x) የለህም እኩያ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection