ምሥጋና የተጋውን እግዚአብሔርን እጠራዋለሁኝ መቅደሱን በዕልልታዪ እበዝማሬ እሞላዋለሁ ይኸው ምሥጋናው ይኸው ዝማሬው ይኸው ዕልልታው ስለሚገባው (2x) የሚሰዋልኝ ለእኔ ምሥጋና እርሱ ያከብረኛል ብሎኛልና ሞላ ጐደለ ሳልል እሰዋለሁ በሙሉ ኃይሌ አመልከዋለሁ አመልከዋለሁ (4x) ነገ ለራሱ ይጨነቅ ይጨነቅ እንጂ እኔስ አርፌ እኖራለሁ በአምላኬ እጅ ነገ ለራሱ ይጨነቅ ይጨነቅ እንጂ እኔስ አርፌ እኖራለሁ በአምላኬ እጅ አዝ፦ ነገሬን በሚያውቅልኝ በእርሱ ላይ እጥላለሁ ትላንትን ያሻገረኝ ለነገም አምነዋለሁ (2x) ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል ያኖረኛል ገና ያሳየኛል ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል ጠላት ዙሪያዬ ሲዞር ይውላል አባባ ቅጥሬን በእሳት ቀጥሮታል አያገነኝም ሌት ቀን ቢለፋ የሚጠብቀኝ ኢየሱስ አያንቀላፋም አያንቀላፋም (4x) አዝ፦ ነገሬን በሚያውቅልኝ በእርሱ ላይ እጥላለሁ ትላንትን ያሻገረኝ ለነገም አምነዋለሁ (2x) ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል ያኖረኛል ገና ያሳየኛል ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል ሃማ በቅናት ሞትን ደግሶ ለመርዶኪዮስ ጉድጓድ ተምሶ መቼ ለጠላት ታልፎ ተሰጠ አምላኩ ደርሶ ነገሩ ተገለበጠ ተገለበጠ (4x) ሰምቼ ነበረ በጆሮዬ ሁሉን ቻይ እንደሆንክ አባብዬ ዛሬም ዐይኔ አይታሃለች ነፍሴ ታመሰግናለች እንደሰማሁ እንዲሁ አየሁ (3x) ሆ እንደሰማሁ እንዲሁ አየሁ (3x) ሆ ከዘለዓለም ፍርድ ከሞት ፍርሃት በደም ኪዳን ነው ነፍሴን የዋጃት በላይ በረከት አንዴ ባርኮኛል ኢየሱስ አለልኝ ኧረ እኔስ ምን ያሰጋኛል ምን ያሰጋኛል (4x) አዝ፦ ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል ያኖረኛል ገና ያሳየኛል ያኖረኛል እርሱ ያሳየኛል