Song Lyrics

ማን ትሉታላችሁ

Yosef Bekele
Kidisina Le Egziabher
ኢየሱስን ማን ትሉታላቹህ ከማንስ ጋር ታስተያዩታላቹህ የእኔን ጌታ ማን ትሉታላቹህ ከየትኛው ታስተያዩታላቹህ እርሱ እኮ ነው ሞትን የረታ ማኅተሙን ብቻውን የፈታ የጌቶቹ ጌታ የጌቶቹ ጌታ (4x) ብዙዎች ነበሩ ኃያል ነን ያሉ ዘመን ሲቀየር እነርሱ ግን የሉ እንዲያው በነበር ቀረ ዝናቸው መቃብር አሉ ሞት ድል ነስቷቸው ሞተ አበቃ አከተመለት እያለ ሰይጣን ሲሳለቅበት ሞት መቼ ያዘው ይህን አንበሳ በሶስተኛው ቀን ኢየሱስ ተነሳ ኢየሱስ ተነሳ (4x) ፍጥረት ይህን ይስማ ይታወቅ እውነቱ ሞትን ድል ያረገ እስኪ ማነው ብርቱ መጽሃፉን ከፍቶ ማኅተሙን የፈታ ኢየሱስ ብቻ ነው አሸናፊ ጌታ አሸናፊ ጌታ (4x) እንደ ጋለ ነሃስ አቤት እግሮቹ እንዴሳት ነበርላብ ናቸው ዐይኖቹ ደረቱን በወርቅ መታጠቂያ ታጥቆ አለ ይኖራል ዘለዓለም ደምቆ ፊቱ ከፀሐይ በላይ ያበራል ግርማ ሞገሱ እጅግ ያስፈራል ይሄ ነው ጌታ እኔ የማመልከው ሰምቶ በእሳት የሚመልሰው የሚመልሰው (4x) ጌታ ነው አቻ የሌለው (4x) አቻ የሌለው (4x) በሠማይ በምድር ከምድርም በታች መቼ ተገኘ መጽሃፉን ከፋች ዮሐንስ ሲያለቅስ ይህንን አይቶ አታልቅስ አለው መላዕኩ መጥቶ መጽሃፉን ሊከፍት ማኅተሙን ሊፈታ ጀግና ተገኝቷል የጌቶች ጌታ ከዳዊት ዘር ግንድ ያቆጠቆጠው የይሁዳ አንበሳ ሁሉን ፈታታው ሁሉን ፈታታው (4x) ጌታ ነው አቻ የሌለው (4x) አቻ የሌለው (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection