እንደበግ ሲነዳ አሁን አልከፈተም ወስደው ሲያንገላቱት አንዳች አልመለሰም (2x) አስጨነቁት በጅራፍ ገረፉት በአደባባይ እርቃኑን ሰቀሉት ቤዛ ሆነ በእኔ ፈንታ ስለእኔ ተመታ ፍቅር ጐልጐታ ላይ ፍቅር ቀራኒዮ ላይ (2x) እዩት እየሲሴን እዩት ስቃዩ ሲያይል እዩት አባብዬን እዩት ሲቃዩ ሲያይል ስቃዩ ሲያይል (4x) ለእኔ ነው ይህ መንከራተቱ ለእኔ ነው ስቃይን ማየቱ ለእኔ ነው ሲዘባበቱበት ለእኔ ነው የበዛው ትዕግሥቱ ለእኔ ነዋ ደፋ ቀና ያለው ለእኔ ነዋ የደም ላብ ያላበው ለእኔ ነዋ ህመሜ ያመመው ለእኔ ነዋ በጦር የተወጋው ለእኔ ለእኔ ለእኔ ነዋ (4x) አባት ሆይ ፈቃድህ ያልከው ይሁን ብሎ መራራውን ጽዋ ጠጣው ተንጠልጥሎ (2x) አፈረሰው የጥሉን ግድግዳ አስታረቀን እኛን ከአብ ጋራ ኢየሱሴ ጣልቃ ገብቶ አንድ አደረገን ሞቶ ለእኔ ነዋ ኤሎሄ ኤሎሄ ለእኔ ነዋ ብሎ የዋተተው ለእኔ ነዋ ጀርባውን በጅራፍ ለእኔ ነዋ የተተለተለው ለእኔ ለእኔ ለእኔ ነዋ (4x) የድካሙን ዋጋ ፍሬውን ሊያይ ታገሰ መስቀል ላይ ሲቀበል ስቃይ (2x) የተናቀ ደግሞም የተጠላ የህማም ሰው መሰለ ተላላ በቁስሎቹ ተፈውሻለሁ ሕይወት አግኝቻለሁ ለእኔ ለእኔ ለእኔ ነዋ (4x)