Song Lyrics

ቅድስና

Yosef Bekele
Kidisina Le Egziabher
ክርስትናን መኖር መኖርን እሻለሁ ጥማቴም ጸሎቴም አንተን ለመምሰል ነው ጌታ ተቀድሶ መኖር መኖርን እሻለሁ አው ጥማቴም ጸሎቴም አንተን ለመምሰል ነው አባ እቀደሳለሁ (3x) ክብርህን ላየው ጌታ እቀደሳለሁ (3x) ፊትህን ላየው አባ እስኪ አግዘኝ አቅም ስጠኝ ለአንተ እንድኖር አስጨክነኝ አስጨክነኝ አስጨክነኝ አስጨክነኝ አባ አስጨክነኝ አዎ ዓለምን በጽድቅህ ስራ እየኮነንኩኝ እህ እይኮነንኩኝ ልኑር አንተን ኢየሱሴን እያስከበርኩኝ አዎ እያስከበርኩኝ ቅዱሱ ስሜ በእኔ ስለተጠራ አባ ስለተጠራ እንዳላሳፍርህ ኢየሱስ እርዳኝ አደራ አዎ እርዳኝ አደራ ጉልበት ስጠኝ አቅም ስጠኝ በጽድቅ እንድኖር አስጨክነኝ አስጨክነኝ አስጨክነኝ አስጨክነኝ አባ አስጨክነኝ አዎ ጨለማ ለዋጣት ዓለም ብርሃን ሆኜ እህ ርሃን ሆኜ ለትውልድ ምሳሌ አርገኝ ልኑር ጨክኜ አዎ ልኑር ጨክኜ መራራውን አጣፋጭ የምድር ጨው አርገኝ አባ የምድር ጨው አርገኝ ሁልጊዜ የጽድቅህ ፍሬ አይታጣብኝ አዎ አይታጣብኝ እስኪ አግዘኝ አቅም ስጠኝ ለአንተ እንድኖር አስጨክነኝ አስጨክነኝ አስጨክነኝ አስጨክነኝ አባ አስጨክነኝ አዎ ቅድስና ለእግዚአብሔር ቅድስና (4x) ለጊዜው ለሚገኝ ደስታ ራሴን አልሸጥም አሃ ራሴምን አልሸጥም ለኑሮ ለእንጀራ ብዬ አልሸቃቅልም አዎ አልሸቃቅልም ይራበኝ እንጂ ልጣ ሁሉ ይቅርብኝ አዎ ሁሉ ይቅርብኝ ጨክኜ ላገለግልህ ወስኛለሁኝ አዎ ወስኛለሁኝ እንደልብህ ልኑርልህ በእኔ ጌታ ደስ ይበልህ ከአንተ ጋራ አሃ እኖራለሁ ክብርህን ላይ ናፍቄያለሁኝ እቀደሳለሁ (3x) ክብርህን ላየው ጌታ እቀደሳለሁ (3x) ፊትህን ላየው አባ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection