በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ለተቀመጥከው (2x) ምሥጋና አምልኮ ይኸው ይዤ መጣሁ ለአንተ ልሰዋ (2x) ቅዱስ ቅዱስ እያልኩኝ ወደ ማደሪያህ እገባለሁኝ ቅዱስ ቅዱስ እያልኩኝ ወደ መቅደስህ እገባለሁኝ አዝ፦ ቅዱስ ነህ ቅዱስ (4x) ቅዱስ ነህ ቅዱስ (4x) ቅዱስ እያሉህ ሲያመልኩ መላዕክቱ ክብርህ ቤቱን ሞልቶት ነበር ኦ አቤቱ እኔም ከልቤ ቅዱስ እያልኩ እጮሃለሁ አንተ ቅዱስ መሆንህን አውጃለሁ አዝ፦ ቅዱስ ነህ ቅዱስ (4x) አመልካሃለሁ ቅዱስ እያልኩኝ እንዳንተ ያለ ስላላየሁኝ ቅዱስ ነህ ቅዱስ (4x) ለዘለዓለም ዙፋንህ ላይ ተቀምጠሃል ደፍሮ ከዙፋንህ ና ውረድ ማን ይልሃል አይቆጠርም ዘመናትህ አንተ ጌታ ቅዱስ እያልኩኝ ልስገድልህ በዕልልታ አዝ፦ ቅዱስ ነህ ቅዱስ (4x) ይደርደርልህ ዛሬም በገናው በዕልልታ ሆታ ቅኔ ምሥጋናው ቅዱስ ነህ ቅዱስ (4x) ስራህ ትክክል እውነተኛ እንከን የለህ ነውር ነቀፋ የሌለብህ አንተ እኮ ነህ ፍርድ አታጓድል አታደላ ጻድቅ አምላክ ነፍሴ ሁልጊዜ በምሥጋና አንተን ትበል አዝ፦ ቅዱስ ነህ ቅዱስ (4x) የጌታዎች ጌታ ጌታ ጌታ የነገሥታት ንጉሥ የአማልክት አምላክ አምላክ አምላክ የእስራኤል ቅዱስ ልዑል እግዚአብሔር ስምህ ይወደስ ስምህ ይቀደስ ዛሬም ልዘለዓለም ይወደስ ክቡር ስምህ (2x) ይቀደስ ክቡር ስምህ (2x) ይወደስ ክቡር ስምህ (2x) ይቀደስ ክቡር ስምህ (2x) ይወደስ ክቡር ስምህ (2x)