አዝ፦ ካለመኖር ወደመኖር ታመጣለህ ቃል ይውጣ እንጂ ምንተስኖህ ትሰራለህ ኢየሱስ ጌታ ነህ (2x) አባቴ ጌታ ነህ (2x) በሞተው ነገር ላይ ነፍስ ህይወትን ዘርተህ (ጌታ እኮ ነህ (2x)) ታኖራለህ ጌታ መቃብርን ከፍተህ (ጌታ እኮ ነህ (2x)) አዋጅን በአዋጅ ስትሽር አይቻለሁ (ጌታ እኮ ነህ (2x)) ታሪክ ተገልብጦ እንዲህ እዘምራለሁ (ጌታ እኮ ነህ (2x)) ጨለማ በፊቴ አይጨልምም ጌታ ነህ ኢየሱስ ለዘለዓለም እኔማ ኧረ እንዴት ዝም እላለሁ ከሞት ያመለጥኩት በአንተ እኮ ነው ጌታ የእኔ ማረፊያ ጌታ መታመኛዬ አዎ ጌታ ስንቱን አለፍኩት ጌታ በአንተ ትምኜው አዝ፦ ካለመኖር ወደመኖር ታመጣለህ ቃል ይውጣ እንጂ ምንተስኖህ ትሰራለህ ኢየሱስ ጌታ ነህ (2x) አባቴ ጌታ ነህ (2x) እንደማያልፍ የለም አለፈ በተራ (ጌታ እኮ ነህ (2x)) እንደፈሳሽ ውኃ ያ ሁሉ መከራ (ጌታ እኮ ነህ (2x)) በዚያ ክፉ ሌሊት ደርሰህ አሳረፍከኝ (ጌታ እኮ ነህ (2x)) ባለውለታዬ አንተው ክበርልኝ (ጌታ እኮ ነህ (2x)) አዝ፦ ካለመኖር ወደመኖር ታመጣለህ ቃል ይውጣ እንጂ ምንተስኖህ ትሰራለህ ኢየሱስ ጌታ ነህ (2x) አባቴ ጌታ ነህ (2x) ለብዙ ዘመናት በዓልጋው ለነበረው (ጌታ እኮ ነህ (2x)) ዘመን መጥቶለታል ለዚያ ለሽባው ሰው (ጌታ እኮ ነህ (2x)) እስርአቱን ፈተህ አዘልለኸዋል (ጌታ እኮ ነህ (2x)) አቤት የእኔ ጌታ ለአንተ ምን ይሳናል (ጌታ እኮ ነህ (2x)) ጨለማ በፊቴ አይጨልምም ጌታ ነህ ኢየሱስ ለዘለዓለም እኔማ ኧረ እንዴት ዝም እላለሁ ከሞት ያመለጥኩት በአንተ እኮ ነው ጌታ የእኔ ማረፊያ ጌታ መታመኛዬ አዎ ጌታ ስንቱን አለፍኩት ጌታ በአንተ ትምኜው አዝ፦ ካለመኖር ወደመኖር ታመጣለህ ቃል ይውጣ እንጂ ምንተስኖህ ትሰራለህ ኢየሱስ ጌታ ነህ (2x) አባቴ ጌታ ነህ (2x)