Song Lyrics

ማነው ታማኝ አገልጋይ

Yosef Bekele
Sintun Lawura
በምድራዊው ጥቅም ነፍሱ ያልታሰረ ክቡሩን አደራ በስራ ያዋለ እራሱን ሸሽጐ አምላኩን ሚያሳይ ማነው በዚህ ዘመን እውነተኛ አገልጋይ (2x) አዝ፦ ማነው ታማኝ አገልጋይ ማነው ትጉህ ኧረኛ ማነው ልባም መጋቢ ማነው እውነተኛ ዳኛ ማነው ፍቅርን የተሞላ ማነው ደግሞም የጸሎት ሰው ማነው ለነፍሳት አሳቢ ማነው እውነት የሚገደው እንዲህ ሲያደርግ ለሚገኘው ከአምላኩ ዘንድ ዋጋ አለው ከጊዜያዊው ይልቅ ሚበልጠውን ሽቶ ዘለዓለማዊውን ከሩቅ ተመልክቶ ትኩር ብሎ ያየ ያንን ብድራቱን በጌታው ያረፈ እውነተኛ ካህን (2x) አዝ፦ ማነው ታማኝ አገልጋይ ማነው ትጉህ ኧረኛ ማነው ልባም መጋቢ ማነው እውነተኛ ዳኛ ማነው ፍቅርን የተሞላ ማነው ደግሞም የጸሎት ሰው ማነው ለነፍሳት አሳቢ ማነው እውነት የሚገደው እንዲህ ሲያደርግ ለሚገኘው ከአምላኩ ዘንድ ዋጋ አለው ነውረኛውን ነገር ጸያፉን የናቀ ከዚህ ዓለም ዝና እራሱን ያራቀ ቅድስናን ለብሶ ለጌታው የሚኖር እግዚአብሔር የጠራው ማነው አምባሳደር (2x) እርዳኝ አባቴ ኦሆሆሆሆ አግባኝ ከቤቴ በሰላም (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection