እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ነው የእኔ ጌታ በዙፋኑ ላይ ነው ማነው የሚመስለው እርሱ ኤልሻዳይ ነው ማነው የሚያክለው እርሱ የበላይ ነው አዎ አዝ፦ ከሁሉ በላይ ነው ጌታ ከሁሉ በላይ በላይ ከሁሉ በላይ ነው ኢየሱስ ከሁሉ በላይ በላይ (2x) በምድር ሁሉ ላይ ገነው የነበሩ እጅግ የከበሩ ደግሞም የተፈሩ ብርቱ ሃያላኖች ጠቢባን ወድቀዋል ብዙዎች ነገሥታት ወድቀው ተረስተዋል የእኛ ግን እግዚአብሔር ዛሬም ክንደ ብርቱ ጉልበቱ ሳይደክም አለ በዙፋኑ በዙፋኑ አለ በዙፋኑ አዎ መቃብር ፈንቅሎ ድል ነስቶ የተነሳ እርሱ ነው ኢየሱስ የይሁዳ አንበሳ (2x) የይሁዳ አንበሳ አዎ አዝ፦ ከሁሉ በላይ ነው ጌታ ከሁሉ በላይ በላይ ከሁሉ በላይ ነው ኢየሱስ ከሁሉ በላይ በላይ (2x) ከሁሉ በላይ በላይ (3x) ናቡከደነጾር ምስል አሰራና ስገዱ አላቸው አምላክ ነው አለና ለምስሉ ከቶ አንሰግዱም ያሉ እነሲድራቅ ታስረው በእቶኑ ተጣሉ ሰባት እጥፍ ሆኖ ቢነድም እሳቱ እርሱን የታመኑ አሸንፈው ወጡ ሃሌሉያ ድል አድርገው ወጡ [1] የነሲድራቅ አምላክ አሁንም ይሰራል ስሙን ለሚጠራው ከሞትም ያድናል ሃሌሉያ ከሞትም ያድናል አዎ ኢየሱስ ጌታ ነው አሃ ኢየሱስ ጌታ ጌታ ኢየሱስ ጌታ ነው ኦሆ ኢየሱስ ጌታ ጌታ (2x) ኢየሱስ ጌታ ጌታ (3x) በጸናችው እጁ ህዝቡን አወጣቸው [2] ባሕሩን አሻግሮ በድንቅ መራቸው [3] ከኋላም ከፊትም ሆኗቸው ከለላ ተስፋውን ወረሱ ቃሉንም አጸና [4] ለእኔማ አባቴ ነው ዛሬም አምነዋለሁ ቢጐድልም ቢሞላም እግዚአብሔር ትልቅ ነው በቁሳቁስ ነገር እኔ አልመዝነውም ከሁሉም ይልቃል ጌታ እኩያ የለውም አባብዬ እኩያ የለውም አዎ አዝ፦ ከሁሉ በላይ ነው ጌታ ከሁሉ በላይ በላይ ከሁሉ በላይ ነው ኢየሱስ ከሁሉ በላይ በላይ (2x) ከሁሉ በላይ በላይ (3x) እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ነው (በዙፋኑ ላይ) የእኔ ጌታ በዙፋኑ ላይ ነው (ኦ ላይ ነው) ማነው የሚመስለው (የእኔ ጌታ) እርሱ ኤልሻዳይ ነው (ማነው ማነው) ማነው የሚያክለው (ኢየሱሴን) እርሱ የበላይ ነው (አዎ አዎ) አዝ፦ ከሁሉ በላይ ነው ጌታ (በላይ በላይ) ከሁሉ በላይ በላይ (በላይ ነው) ከሁሉ በላይ ነው ኢየሱስ (በላይ በላይ) ከሁሉ በላይ በላይ (2x) ከሁሉ በላይ በላይ (3x)