Song Lyrics

እንዳንተ ያለ

Yosef Bekele
Sintun Lawura
አዝ፦ እንዳንተ ያለ (3x) አባቴ ለእኔስ ከቶ ማን አለ እንዳንተ ያለ (3x) ኢየሱሴ ለእኔስ ከቶ ማን አለ ኦ መዳኔ እጅግ ይደንቀኛል የፍቅርህ ብዛቱ እንዲህ ያዘምረኛል ውለታህ መች ዝም ያሰኛል (3x) ላውራ ማዳንህን ጌታ ላውራ ስራህን ኢየሱስ (2x) ተስፋ ቆርጬ ሌት ቀን ሳነባ መድረሻ ጠፍቶኝ ሆኜ እምባ በእምባ እንዳንተ ማነው የደረሰልኝ እምባዬን ጠርጐ ና ልጄ ሆይ ያለኝ አዝ፦ እንዳንተ ያለ (3x) አባቴ ለእኔስ ከቶ ማን አለ እንዳንተ ያለ (3x) ኢየሱሴ ለእኔስ ከቶ ማን አለ ጐልያድ በፊቴ እንዲያው ተደንቅሮ ባስጨነቀኝ ቁጥር ሳሰማ እሮሮ ኧረ እንዳንተ ማነው ከተፍ ያለልኝ ያንን ተራራውን ከፊቴ ጣለልኝ አዝ፦ እንዳንተ ያለ (3x) አባቴ ለእኔስ ከቶ ማን አለ እንዳንተ ያለ (3x) ኢየሱሴ ለእኔስ ከቶ ማን አለ በጨነቀኝ ጊዜ ጌታ አንተን ጠራሁህ መታመኛዬ ሆይ ወዴት ነህ አልኩህ አንተም አልናከኝም ቃሌን ሁሉ ሰማህ ምሥጋና ውዳሴ ክብር ይሁንልህ አዝ፦ እንዳንተ ያለ (3x) አባቴ ለእኔስ ከቶ ማን አለ እንዳንተ ያለ (3x) ኢየሱሴ ለእኔስ ከቶ ማን አለ ኦ መዳኔ እጅግ ይደንቀኛል የፍቅርህ ብዛቱ እንዲህ ያዘምረኛል ውለታህ መች ዝም ያሰኛል (3x) ላውራ ማዳንህን ጌታ ላውራ ስራህን ኢየሱስ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection