Song Lyrics

ወዶኛል እና አዳነኝ

Yosef Bekele
Sintun Lawura
ቸርነቱን ለእኔ ሁሌ እዘምራለሁ የአባትነት ፍቅሩን ቀምሼ ስላየሁ ጐልጐታ አናት ላይ ለእኔ ሞቶልኛል የኀጢአት እስራቴን በጥሶ ጥሎታል (2x) አዝ፦ ወዶኛልና አዳነኝ (2x) ምህረቱ ሰው አደረገኝ (3x) ወዶኛልና አዳነኝ (2x) ምህረቱ ሰው አደረገኝ (3x) ከሰማይ ሰማያት ከዙፋኑ ወርዶ ሁሉን ስለፍቅር አደረገ ባዶ መስቀል ተሸክሞ ደፋ ቀና ያለው ያ ሁሉ ስቃዩ ለእኔ ነው ለእኔ ነው (2x) አዝ፦ ወዶኛልና አዳነኝ (2x) ምህረቱ ሰው አደረገኝ (3x) አደባባይ ቆመ እርቃኑን ስለ እኔ አላፈረብኝም ኢየሱስ መድኅኔ በእኔ ፈንታ ሞቶ እኔን አድኖኛል በከበረው ደሙ ጌታዬ ዋጅቶኛል (2x) አዝ፦ ወዶኛልና አዳነኝ (2x) ምህረቱ ሰው አደረገኝ (3x) የምህረት መግቢያ በሩ ተክፈተ የጥሉ ግድግዳ በደሙ ፈረሰ ተፈጸመ ብሎ ሁሉን ጨርሶታል ሞትና ሲዖልን ድል ነስቶ ተነስቷል (2x) አዝ፦ ወዶኛልና አዳነኝ (2x) ምህረቱ ሰው አደረገኝ (6x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection