Song Lyrics

ስንቱን ላውራ

Yosef Bekele
Sintun Lawura
በመከራዬ ቀን አልተለየኸኝም አበሳዬን ከኔ ላራቀልኝ ለዚህ ለጌታዬ እሰግዳለሁ ሁልጊዜ ምሥጋናን አበዛለሁ ዘምርለታለሁ (5x) ለአባቴ ዘምርለታለሁ አዝ፦ ስንቱን ላውራው ልተርከው አንተ ያደረከው ከአይምሮ በላይ ነው ጌታ ከአይምሮ በላይ ነው (4x) ፊትለፊት ቆሞ ከፍ ያለ ተራራ የመድሃኒቴ አምላክ ስልህ ሰማኸኝ ስጣራ በተራራዬ ላይ በድል አራመድከኝ ከሳሶቼ እያዩ አሜን ተስፋዬን ወረስኩታ ተስፋዬን ሰበርኩት አዝ፦ ስንቱን ላውራው ልተርከው አንተ ያደረከው ከአይምሮ በላይ ነው ጌታ ከአይምሮ በላይ ነው (4x) ተስፋዬን ቆርጬ ለሰው ያልነገርኩት አበቃለት ብዬ ሞቶ የቀበርኩት ምንተስኖህ ጌታ ሁሉ ተችሎሃል አንገት ያስደፋኝን ቀንበሬን ሰብረሃል ጌታ ቀንበሬን ሰብረሃል አዝ፦ ስንቱን ላውራው ልተርከው አንተ ያደረከው ከአይምሮ በላይ ነው ጌታ ከአይምሮ በላይ ነው (4x) አዋጅ ሲል ጠላቴ እኔን ሊያጠፋ ከበሮ ሲያስደልቅ ነጋሪት ሲያስመታ በአንድ ሌሊትይ ጀምበር ታሪክ ተቀየረ ጠላት በቆፈረው አሜን ጉድጓድ ተቀበረ እሰይ ጉድጓድ ተቀበረ በመከራዬ ቀን አልተለየኸኝም (አልተለየኸኝም) አበሳዬን ከኔ ላራቀልኝ (ላራቀልኝ) ለዚህ ለጌታዬ እሰግዳለሁ ሁልጊዜ ምሥጋናን አበዛለሁ ዘምርለታለሁ አዎ ዘምርለታለሁ (ዘምርለታለሁ) (2x) ዘምርለታለሁ ለአባቴ ዘምርለታለሁ (አቤት አቤት) አዝ፦ ስንቱን ላውራ (ላውራ) ልተርከው (ልተርከው) አንተ ያደረከው (ያደረከው) ከአይምሮ በላይ ነው ጌታ (በላይ በላይ ነው) ከአይምሮ በላይ ነው (4x) (በላይ በላይ)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection