አዝ፦ ጉድለቴን ሸፍነህ እዚህ አደረስከኝ ያን ሁሉ ሸለቆ አዝለህ ያሻገርከኝ ኢየሱሴ ተባረክልኝ (2x) አባብዬ ተባረክልኝ (2x) ማዳን በማይችሉት እኔስ አልመካም አንተ ብቻ እኮ ነህ የሕይወቴ ጌታ አንተ ነህ (2x) አንተ እኮ ጌታ አንተ ነህ (2x) አንተ እኮ ጌታ አንተ እኮ ጌታ (2x) አንተ ብቻ ጌታ (2x) ከንጉሥ ገበታ የማይገባኝን (2x) ሁሉ በድካሜ የተጸየፈኝን (2x) ከማዕድን መሃል አስቀምጠኸኛል (2x) ኦ ኢየሱሴ ፍቅርህ እኔን ሰው አድርጐኛል ምን ብል ያረካኛል ተባረክልኝ (3x) አባቴ ተባረክልኝ ከፍ በልልኝ (3x) ኢየሱሴ ከፍ በልልኝ አዝ፦ ጉድለቴን ሸፍነህ እዚህ አደረስከኝ ያን ሁሉ ሸለቆ አዝለህ ያሻገርከኝ ኢየሱሴ ተባረክልኝ (2x) አባብዬ ተባረክልኝ (2x) ተራራ ስወጣ ጉልበት እየሆንከኝ (2x) ስወድቅ ስነሳ እየደጋገፍከኝ (2x) አቤት በአንተ ብርታት ስንቱን አልፌያለሁ (2x) በምህረትህ ብዛት እዚህ ደርሻለሁ ዛሬ ደርሻለሁ ተባረክልኝ (3x) አባቴ ተባረክልኝ ከፍ በልልኝ (3x) ኢየሱሴ ከፍ በልልኝ ትላንትን አልፌ እዚህ እኮ መድረሴ በአንተ ብርታት እንጂ አይደለም በራሴ (2x) ትላንትን አልፌ እዚህ እኮ መድረሴ በአንተ ብርታት እንጂ አይደለም በራሴ (2x) አይደለም በራሴ በራሴ አይደለም በራሴ (2x) አዝ፦ ጉድለቴን ሸፍነህ እዚህ አደረስከኝ ያን ሁሉ ሸለቆ አዝለህ ያሻገርከኝ ኢየሱሴ ተባረክልኝ (2x) አባብዬ ተባረክልኝ (2x)