አዝ፦ እግዚአብሔር አላማዬ ነዉ ( 2x) ጠላት የሚለኝን ለምንስ ልስማዉ ልውጣ ልሄድ ልውረሰዉ አዎ ( 2x) አላማ ያላቸው የጥንት አባቶቼ ድል አደረጉ እንጂ ተሸነፉ መቼ እኔም አላማዬን አንተን አድርጌያለሁ የጠላቶቼን ደጅ በእምነት እወርሳለሁ እወርሳለሁ እወርሳለሁ (፬x) አማሌቅ በፊቴ ሆኖ ቢያቅራራ ምን ትልቅ ቢመስል እኔ እንደው አልፈራ የአምላኬን ስም ይዤ በእምነት እወጣለሁ ጠላቴን ከእግሬ ስር አጋድመዋለሁ አምላኬ ሃይሌ ነው እኔ አልፈራም አልፈራም ( 2x) እኔ አልሰጋም አልሰጋም ( 2x) አዝ፦ እግዚአብሔር አላማዬ ነዉ ( 2x) ጠላት የሚለኝን ለምንስ ልስማዉ ልውጣ ልሄድ ልውረሰዉ አዎ ( 2x) እንደ ሰናኦር ግምብ ቢቆምም በፊቴ ይደባልቀዋል ቋንቋውን አባቴ ምርኮን በምርኮ ላይ ይጨምርልኛል ያመንኩት ጌታዬ መቼ ይተወኛል ( 2x) እኔ አልፈራም አልፈራም ( 2x) እኔ አልሰጋም አልሰጋም ( 2x) የድል ሰንደቄ ነው የሕይወቴ አርባ አሃሃ እኔ የማመልከው ጌታ ባለግርማ ባለግርማ ኢየሱስ ባለግርማ ( 2x)