Song Lyrics

ከለላዬ

Yosef Bekele
Sintun Lawura
አዝ፦ እግዚአብሔር አላማዬ ነዉ (2x) ጠላት የሚለኝን ለምንስ ልስማዉ ልውጣ ልሄድ ልውረሰዉ አዎ (2x) አላማ ያላቸው የጥንት አባቶቼ ድል አደረጉ እንጂ ተሸነፉ መቼ እኔም አላማዬን አንተን አድርጌያለሁ የጠላቶቼን ደጅ በእምነት እወርሳለሁ እወርሳለሁ እወርሳለሁ (4x) አማሌቅ በፊቴ ሆኖ ቢያቅራራ ምን ትልቅ ቢመስል እኔ እንደው አልፈራ የአምላኬን ስም ይዤ በእምነት እወጣለሁ ጠላቴን ከእግሬ ስር አጋድመዋለሁ አምላኬ ሃይሌ ነው እኔ አልፈራም አልፈራም (2x) እኔ አልሰጋም አልሰጋም (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር አላማዬ ነዉ (2x) ጠላት የሚለኝን ለምንስ ልስማዉ ልውጣ ልሄድ ልውረሰዉ አዎ (2x) እንደ ሰናኦር ግምብ ቢቆምም በፊቴ ይደባልቀዋል ቋንቋውን አባቴ ምርኮን በምርኮ ላይ ይጨምርልኛል ያመንኩት ጌታዬ መቼ ይተወኛል (2x) እኔ አልፈራም አልፈራም (2x) እኔ አልሰጋም አልሰጋም (2x) የድል ሰንደቄ ነው የሕይወቴ አርባ አሃሃ እኔ የማመልከው ጌታ ባለግርማ ባለግርማ ኢየሱስ ባለግርማ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection