አዝ፦ ነፍሴ ምሥጋናህን ታመጣለች አባት ከአንተ ሌላ የለም ትላለች ውለታህ ብዙ ነው የእኔ ጌታ ልስገድ ልገዛልህ ጥዋት ማታ ልስገድ ልገዛልህ ጥዋት ማታ ጋሻዪ አንተ ነህ የእኔ ጌታ በምሥጋና ሆ እያልኩኝ በድል ዛሬም እሄዳለሁኝ ዘምራለሁ በታላቅ ዜማ አዳኝ የለም ከአንተ ሌላ ከአንተ ሌላ (4x) ማን አየው ያንን ብሶቴን ማን ሰማው ብርቱ ለቅሶዬን ጩኸቴን ሰምተህ ደረስህ እምባዬን ከዐይኔ አበስህ እንደአንተ ያለ አላየሁም እንደአንተ ያለ አልሰማሁም ኢየሱሴ የእኔ አለኝታ ክበር በዕልልታ ወድሃለሁኝ ጌታዬ ወድሃለሁኝ ወድሃለሁኝ ኢየሱሴ ወድሃለሁኝ ወድሃለሁኝ አባቴ ወድሃለሁኝ ወድሃለሁኝ ወዳጄ ወድሃለሁኝ አዝ፦ ነፍሴ ምሥጋናህን ታመጣለች አባት ከአንተ ሌላ የለም ትላለች ውለታህ ብዙ ነው የእኔ ጌታ ልስገድ ልገዛልህ ጥዋት ማታ ልስገድ ልገዛልህ ጥዋት ማታ ጋሻዪ አንተ ነህ የእኔ ጌታ በምሥጋና ሆ እያልኩኝ በድል ዛሬም እሄዳለሁኝ ዘምራለሁ በታላቅ ዜማ አዳኝ የለም ከአንተ ሌላ ከአንተ ሌላ (4x) ጓዳዬን ሁሉ ታያለህ በቤቴ ውስጥ ትገባለህ ባጣ እንኳን አትርቀኝም ሰንፈህ ችላም አትለኝም አሳዳጊ ነህ መመኪያዬ ቸር ወዳጅ ውዱ ጌታዬ አቤት ኢየሱስ ምን ልበልህ ይባረክ ስምህ አዎ ወድሃለሁኝ ጌታዬ ወድሃለሁኝ ወድሃለሁኝ ኢየሱሴ ወድሃለሁኝ ወድሃለሁኝ አባቴ ወድሃለሁኝ ወድሃለሁኝ ወዳጄ ወድሃለሁኝ አዝ፦ ነፍሴ ምሥጋናህን ታመጣለች አባት ከአንተ ሌላ የለም ትላለች ውለታህ ብዙ ነው የእኔ ጌታ ልስገድ ልገዛልህ ጥዋት ማታ ልስገድ ልገዛልህ ጥዋት ማታ ጋሻዪ አንተ ነህ የእኔ ጌታ በምሥጋና ሆ እያልኩኝ በድል ዛሬም እሄዳለሁኝ ዘምራለሁ በታላቅ ዜማ አዳኝ የለም ከአንተ ሌላ ከአንተ ሌላ (4x) ብቸኝነት ሲያስመርረኝ ባይተዋርነት ሲያጠቃኝ ተገን የሆንከኝ ረዳቴ አንተ ነህ ውዱ አባቴ ቀርበኸኝ በመከራዬ አገዝከኝ ጣልከው ሸክሜን ወንድም መከታ ኢየሱስ ዘለዓለም ንገሥ አዎ ወድሃለሁኝ ጌታዬ ወድሃለሁኝ (ወድሃለሁኝ) ወድሃለሁኝ ኢየሱሴ ወድሃለሁኝ (ኦ ወድሃለሁኝ) ወድሃለሁኝ አባቴ ወድሃለሁኝ (ወድሃለሁኝ) ወድሃለሁኝ ወዳጄ ወድሃለሁኝ አዝ፦ ነፍሴ ምሥጋናህን ታመጣለች አባት ከአንተ ሌላ የለም ትላለች ውለታህ ብዙ ነው የእኔ ጌታ (ልስገድ) ልስገድ ልገዛልህ ጥዋት ማታ (ልስገድ) ልስገድ ልገዛልህ ጥዋት ማታ (አሃሃ) ጋሻዪ አንተ ነህ የእኔ ጌታ በምሥጋና ሆ እያልኩኝ በድል ዛሬም እሄዳለሁኝ ዘምራለሁ በታላቅ ዜማ አዳኝ የለም ከአንተ ሌላ ከአንተ ሌላ (4x)