አዝ፦ የሰራዊት አምላክ ሆይ ማደሪያህ እንዴት ድንቅ ነው ማደሪያህ እንዴት ልዩ ነው ማደሪያህ የተወደደ ነው አዎ (2x) ነፍሴ አንተን አደባባዮችህ ወደደችህ አሃሃሃ ወደደችህ አዎ (2x) አእላፋት መላእክት በፊትህ ቅድስናህን ሚያውጁልህ ዙፋንህ ቅዱስ ነው ገናና በምሥጋናም የተፈራህ ድምጽህ እንደብዙዎች ነው ቃልህ ከማር እልቅ ጣፋጭ ነው በምክርህ ግሩም ነህ ጌታዬ ዙፋኑ የአንተ ነው የልቤ በምክርህ ግሩም ነህ ጌታዬ ዛሬም ሾሜሃለሁ በላዬ አዝ፦ የሰራዊት አምላክ ሆይ ማደሪያህ እንዴት ድንቅ ነው ማደሪያህ እንዴት ልዩ ነው ማደሪያህ የተወደደ ነው አዎ (2x) ነፍሴ አንተን አደባባዮችህ ወደደችህ አሃሃሃ ወደደችህ አዎ (2x) አቤቱ ውበትህ ያማረ እኔስ አላየሁም እንደአንተ ፍጥረት ተደነቀ በስራህ አቤት የእኔስ ጌታ ልዩ ነህ በትንሿ ልቤ ገብተሃል ማደሪያ ቤትህ አድርገሃል አኔም ሁልጊዜ ላምልክህ ኢየሱስ ጌታዬ ልበልህ እኔም ሁልጊዜ ላክብርህ ኢየሱስ ጌታዬ ልበልህ ኢየሱሴ ጌታዬ አምባዬ ጋሻዬ እውነተኛ ወዳጅ እንደአንተ ማነው በጨለማው ሌሊት ፈጥኖ ሚደርሰው ነፍሴ አንተን ባርኮ አጸለችም ክበር የእኔ ጌታ ለዘለዓለም (2x) አምላኬ አሃ ያደረከው ነገር ለእኔ የሰራኸው ስራ በዘመኔ ቢነገር ቢነገር ስጦታህ መች ያልቃል ጌታዪ ደግነትህ መች ያልቃል አባትዬ ደግነትህ ባወራው ባወራው ስጦታህን መች ያልቃል ኢየሱስዬ በጐነትህ መች ያልቃል ወዳጄ በጐነትህ