Song Lyrics

ቸርነትህን አዜማለሁ

Yosef Bekele
Mahitemen Yefetah
አዝ፦ አቤቱ አምላኬ ድንቅ ነህ ቃላቶች ያጥሩኛል የምልህ ምሥጋናን ሁልጊዜ አበዛለሁ ቸርነትህን አዜማለሁ አምላኬ አንተን የእኔ ጌታ እገዛልሃለሁ ጠዋት ማታ አባቴ አንተን የእኔ ጌታ እኔ አመልክሃለሁ በደስታ ተስፋ ያደረኩት ያመንኩት ሲከዳኝ አስፈሪው ጨለማም ዙሪያዬን ሲከበኝ ነፍሴ ስትጨነቅ ደረስህ ወዳጄ ጨለማዬም በራ ተዋበልኝ ደጄ ላንግስህ ሰግቼ ኢየሱስ ላንግስህ ሰግቼ አዝ፦ አቤቱ አምላኬ ድንቅ ነህ ቃላቶች ያጥሩኛል የምልህ ምሥጋናን ሁልጊዜ አበዛለሁ ቸርነትህን አዜማለሁ አምላኬ አንተን የእኔ ጌታ እገዛልሃለሁ ጠዋት ማታ አባቴ አንተን የእኔ ጌታ እኔ አመልክሃለሁ በደስታ የተሰበረውን ስብራቱን ጠጋኝ የታመመን ፈዋሽ ያዘነውን አጽናኝ ከእናት ከአባት በላይ ደርሰህ ትረዳለህ የምስኪኑ አባት መጠጊያው አንተ ነህ ዛሬም ላሞጋግስህ ኢየሱስ ዛሬም ላሞጋግስህ አዝ፦ አቤቱ አምላኬ ድንቅ ነህ ቃላቶች ያጥሩኛል የምልህ ምሥጋናን ሁልጊዜ አበዛለሁ ቸርነትህን አዜማለሁ አምላኬ አንተን የእኔ ጌታ እገዛልሃለሁ ጠዋት ማታ አባቴ አንተን የእኔ ጌታ እኔ አመልክሃለሁ በደስታ ወደላይ ብወጣም አንተ በዚያ አለህ ወደታች ብወርድም በዚያም ትገኛለህ በምድር ስፋት ሁሉ ያለውን የምታይ እንደአንተ ማን አለ የሚኖር በሰማይ አንተ ነህ የበላይ ጌታ አንተ ነህ የበላይ አዝ፦ አቤቱ አምላኬ ድንቅ ነህ ቃላቶች ያጥሩኛል የምልህ ምሥጋናን ሁልጊዜ አበዛለሁ ቸርነትህን አዜማለሁ አምላኬ አንተን የእኔ ጌታ እገዛልሃለሁ ጠዋት ማታ አባቴ አንተን የእኔ ጌታ እኔ አመልክሃለሁ በደስታ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection