መከራ ሲበዛ ቀንም ሲጨላልም ኢየሱስ አንተ ነህ የምትሆን ወንድም አዎ የተዘጋውን በር ደርሰህ ትከፍታለህ ከድሃው ጐን ኢየሱስ ትቆምለታለህ አዎ የምስኪኖች ወዳጅ ኢየሱስ የተጣለን ምታነሳ ቸር አምላክ??? በክብር ምታኖር አበሳውን ምታስረሳ አቤት አቤት ጌታዬ እንደአንተ ያለ እውነተኛ ወዳጅ ማንም የለም (አቤት አቤት) አቤት አቤት አባባ እንደአንተ ያለ እውነተኛ ወዳጅ ማንም የለም አዎ አንተው ብቻ አባቴ ነህ አንተው ብቻ ጌታ አንተው ብቻ ወዳጄ ነህ አንተው ብቻ ጌታ አንተው ብቻ አሃሃ አንተው ብቻ አዎ አንተው ብቻ እውነተኛ አንተው ብቻ ኢየሱስ ዘመን ቢከፋም እኔስ አምንሃለሁ አንተ እኮ ከያዝከኝ እንዳልወድቅ አውቃለሁ አዎ የማምለጫ አለት መሸሻ አምባዬ የክፉ ቀን ወዳጅ ለእኔስ መጠጊያዬ አዎ ዝርግፍ ጌጤ ምኮራብህ አለኝ ብዬ ምመካብህ አንተው ብቻ የእኔ ወዳጅ በራሴ ላይ ዛሬም ሾምኩህ አቤት አቤት ኢየሱሴ እንደአንተ ያለ እውነተኛ ወዳጅ ማንም የለም (አቤት አቤት) አቤት አቤት አባቴ እንደአንተ ያለ እውነተኛ ወዳጅ ማንም የለም አዎ አንተው ብቻ መኩራዬ ነህ አንተው ብቻ ጌታ አንተው ብቻ ዝርግፍ ጌጤ አንተው ብቻ ጌታ አንተው ብቻ አሃሃ አንተው ብቻ ኢየሱስ አንተው ብቻ እውነተኛ አንተው ብቻ ኢየሱስ ሰባራውን ልቤን አንተው ጠገንክልኝ ሸክሜን ከላይ አንከባለልክልኝ አዎ ዛሬ ይኸው ቀና አልኩኝ በአንተ የእኔ ጌታ አርነት ወጣሁኝ መቆዘኔ አበቃ አዎ የልቤ ወዳጅ ሚስጥረኛ የጓዳዬን ምታውቅልኝ አቤት በአንተ ስንቱን አለፍኩ ኢየሱሴ ክበርልኝ አቤት አቤት ጌታዬ እንደአንተ ያለ እውነተኛ ወዳጅ ማንም የለም (አቤት አቤት) አቤት አቤት አባባ እንደአንተ ያለ እውነተኛ ወዳጅ ማንም የለም አዎ በመከራዬ ቀን ለቅሶዬን ሰምተሃል እምባዬን አብሰህ ሳቅ አርገህልኛል አስጨናቂዎቼ ዛሬ ይኸው አፈሩ አንተ የሰራኸውን ማዳንህን አዩ አዎ ማን እንደአንተ የእኔ ኢየሱስ እስራትን የሚፈታ ቀንበር ሰብሮ የሚያሳርፍ ለቅሶውን ደግሞ በደስታ አቤት አቤት ኢየሱሴ እንደአንተ ያለ እውነተኛ ወዳጅ ማንም የለም (አቤት አቤት) አቤት አቤት አባባ እንደአንተ ያለ እውነተኛ ወዳጅ ማንም የለም አዎ ቸርነትህን ምህረትህን በሕይወቴ አይቻለሁ ራራህልኝ የእኔ ጌታ ያለፈውን ረስቻለሁ ስብራቴን ጠግነኸው ቀና አድርገህ አራመድከኝ ቁሻሻዬን አስወግደህ ንጹህ ልቤስን አለበስከኝ አንተው ብቻ ግነህልኝ የእኔ ኢየሱስ ግነህልኝ ዛሬም አንተው ነህ መኩራዬ የዘለዓለም ማረፊያዬ ምሥጋና ምሥጋና ዛሬም እንደገና ለጌታ ለአምላኬ ይገባዋልና ምሥጋና ምሥጋና ዛሬም እንደገና ለጌታ ለአባቴ ይገባዋልና ኢየሱሴ የእኔ ጌታ ጉልበቴ ነህ እወድሃለሁ አንተ አለቴ መድሃኒቴ አምባዬ ነህ አመልክሃለሁ ስትረዳኝ ስታግዘኝ ስታጽናናኝ አየሁ በዐይኔ ምን እላለሁ ማዳንህን አወራለሁ በዘመኔ አንተው ብቻ ግነህልኝ??? የእኔ ኢየሱስ ግነህልኝ ዛሬም አንተው ነህ መኩራዬ የዘለዓለም ማረፊያዬ ምሥጋና ምሥጋና ዛሬም እንደገና ለጌታ ለአምላኬ ይገባዋልና ምሥጋና ምሥጋና ዛሬም እንደገና ለጌታ ለአባቴ ይገባዋልና ብርና ወርቅ አልማዝ ዕንቁ ቀይም ዘምቤል አያክል ለእኔ እኮ አንተ ከዚም በላይ ታበራለህ ውብ እኮ ነህ ደም ግባቴ ዛሬም ጥርሴ ሞገሴ ነህ የእኔ ጌታ ላመስግንህ በዝማሬ በሆታና በዕልልታ አንተው ብቻ ግነህልኝ የእኔ ኢየሱስ ግነህልኝ ዛሬም አንተው ነህ መኩራዬ የዘለዓለም ማረፊያዬ ሃሌሉያ ምሥጋና ምሥጋና ዛሬም እንደገና ለጌታ ለአምላኬ ይገባዋልና ምሥጋና ምሥጋና ዛሬም እንደገና ለጌታ ለአባቴ ይገባዋልና