Song Lyrics

የማዕዘን ራስ

Yosef Bekele
Kidisina Le Egziabher
ኢየሱስ ከስም ሁሉ በላይ ስሙ ኃያል ጉልበት ሁሉ ፊቱ ተንበርክኮ ለእርሱ ይሰግዳል አይቆምም ማንም ፊቱ እሳት ነው ለጠላቱ አምላኬ ክንደ ብርቱ ኢየሱስ ክንደ ብርቱ የሱሴ ክንደ ብርቱ ጌታዬ ክንደ ብርቱ ኢየሱሴ ክንደ ብርቱ አሃ ለተቀበሉት አሃ በእርሱ ለሚያምኑት የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣን ሰጣቸው ጌታዬ ስልጣን ሰጣቸው ኢየሱስ ስልጣን ሰጣቸው ጌታዬ ስልጣን ሰጣቸው አሃ ስልጣን ሰጣቸው ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን እራስ ሆነ እርሱ የማዕዘን እራስ እርሱ የማዕዘን እራስ ሆነ እርሱ የማዕዘን እራስ ከስም በላይ ስምን ሰጥቶ እግዚአብሔር ያለልክ ያከበረው ኢየሱስ እርሱ ጌታዪ ነው ኢየሱስ እርሱ ንጉሤ ነው ኢየሱስ እርሱ አባቴ ነው ኢየሱስ እርሱ አዳኜ ነው ያድናል የሚጠራውን ያድናል የታመነውን ያድናል በልቡ ዙፋን ያድናል ያነገሠውን ኢየሱስ ከሞት የማምለጫ ጽኑ አለት ሰው ሁሉ ስሙን እየጠራ ሚድንበት ሕይወት ነው የዘለዓለም የሚያድን ከጠፊው ዓለም ከእርሱ በቀር ማንም የለም ሕይወት ነው የዘለዓለም ከእሱ በቀር አዳኝ የለም ንጉሥ ነው ለዘለዓለም ከእርሱ በቀር አዳኝ የለም አሃ ለተቀበሉት አሃ በእርሱ ለሚያምኑት የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣን ሰጣቸው ጌታዬ ስልጣን ሰጣቸው ኢየሱስ ስልጣን ሰጣቸው ጌታዬ ስልጣን ሰጣቸው አሃ ስልጣን ሰጣቸው ይሄ ስም ነው መዳኛዬ በክፉ ቀን ማምለጫዬ ኢየሱስ ነው መዳኛዬ በክፉ ቀን ማምለጫዬ (3x) ከእርሱ በቀር ሌላ ላላይ ሌላ ሌላ ላላይ ሾሜዋለሁ በላዬ ላይ እኔስ በላዬ ላይ ሌላ ሌላ ላላይ (ሌላ ሌላ ላላይ) (6x) ሃገሬ (Hagerie) ዮሴፍ በቀለ እሄዳለሁ ሃገሬ ጌታዬን አየዋለሁኝ ላየው ፊትለፊቱ ሃገር አለኝ እኔስ በሠማያት በጉ ብርሃኗ የሆነላት የሆነላት ሃገር አለኝ እኔስ በሠማያት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ያዘጋጃት (3x) እንግዳ ነኝና አልሆንም ቤተኛ (2x) ሃገሬ ሠማይ ነው በላይ ርስት አለኛ በላይ ቤት አለኛ ተዘጋጅቼ ልጠብቀው ቤቴን ሌት ተቀን ላሰናዳው ይመጣል ጌታ ይመጣል ይመጣል እርሱ ይመጣል (2x) አሃሃሃ አልዘናጋም አሃሃሃ ጠፊውን አይቼ አሃሃሃ በላዬ ላከማች አሃሃሃ ልስራ ተግቼ አሃሃሃ እርሱ ይመጣል አሃሃሃ ወይ እሄዳለሁ አሃሃሃ እንደስራዬ አሃሃሃ እቀበላለሁ ዐይን ያላያት የሰው እጅ ያልሰራት ለልጆቹ ጌታ ያዘጋጃት ሃገር አለኝ እኔስ በሠማይ (2x) የቅዱሳን የጻድቃን ከተማ ቀኑ ቀርቧል ወደዚያ ልገባ ሃገር አለኝ እኔስ በሠማይ (2x) መታረት መራቆት መራብም ያልፍና ሰቆቃው ሃዘኑ ሁሉ ይረሳና ጌታዬን ፊትለፊት በክብር አያለሁ ናፍቆቴን ደስታዬን ያኔ እወጣለሁ ይመጣል ጌታ ይመጣል ይመጣል እርሱ ይመጣል (2x) የፍጻሜው መለከት ይነፋል ጌታ ኢየሱስ በክብር ይመጣል ሃገር አለን እኛስ በሠማይ (2x) በቅጽበት ዐይን ሁሉ ይለወጥና እንሄዳለን ልንኖር ከእርሱ ጋራ ሃገር አለን እኛስ በሠማይ (2x) የዚህ ዓለም ነገር አላፊ ጠፊ ነው ውበት ደም ግባትም ሁሉ ረጋፊ ነው ጌታዬ ሲመጣ እንዳየው ሳላፍር ሥጋዪን ልጐስም ልኑር ለእርሱ ክብር ይመጣል ጌታ ይመጣል ይመጣል እርሱ ይመጣል (2x) እዚህ ነዋሪ አይደለሁም አይደለሁም እንግዳ ነኝ እኔ ቆይታዬ ያበቃና ይፈጸማል እሄዳለሁ ሃገሬ ሃገሬ በሠማይ ሃገሬ ሃገሬ በላይ ነው ሃገሬ ሃገሬ በሠማይ ሃገሬ ሃገሬ በላይ ነው ሃገሬ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection