ጓዳዬ ሆኜ የልቤን ነገርኩት የውስጥ የሆዴን በጊዜው ጌታ መጣና አሳመረልኝ ድንቅ አረገና (2x) አሳመረለኝ አሃሃ ድንቅ አረገና (2x) አሳመረልኝ አዎ ድንቅ አረገና (2x) ጌታ እኮ ነው የራራልኝ የራራልኝ ያንን ዘመን ያሻገረኝ ያሻገረኝ ዘምራለሁ ለዚህ ጌታ ያረገልኝ ብዙ ነው የእርሱ ውለታ ይዤ ልግባ ማደሪያው ምሥጋናዬ ያውድ መዓዛው ያውድ መዐዛው ይብዛ ዕልልታው (2x) በማደሪያው ምሥጋናው በማደሪያው ዕልልታው በመቅደሱ ምሥጋናው በመቅደሱ ዕልልታው አላስኬድ ያሉኝ ከፊቴ ቆመው ህልሜን ተስፋዬን ሁሉ አጨልመው መንገዴን ዘግተው በቆሙት ላይ ቁጣው ነደደ መጣ ከላይ በበቀል እሳት ወረደባቸው ግድብ እንዲፈርስ አፈረሳቸው አፈረሳቸው (2x) እኔማ ጌታን ብዬ አላፈርኩ እርሱን ብዬ ጨመረ ምሥጋናዬ (2x) ጨመረ ምሥጋናዬ (2x) ለእንቆቅልሼ መፍትሄ ሰጥቶ የሚያስፈነድቅ የልብን ሞልቶ ከአፉ ከወጣ ስልጣን ያለው ቃል የማይሆን የለም ያለው ይሆናል እንደርሱ ማነው ተዐምረኛ እንቆቅልሼን ፈቶ አሳየኛ ፈቶ አሳየኛ (2x) ተሰርቶልኝ ስራዬ ሃዘን ሄዷል ከላዬ ቤቴን ሞላው ደስታ ልዘምር ለዚህ ጌታ (2x) ልዘምር ለዚህ ጌታ (4x) ፍጥረት በስራህ የሚገዙለት ማዕበል ወጀቡ የሚታዘዙለት ይናገር እንጁ ይበል ንጉሡ ማይሰማው የለም ሕያው ግዑዙ እርሱ ነው ጌታ ዐይኔ አይቶታል ማይቻለውን ሁሉ ችሎታል ሁሉ ችሎታል (2x) እኔማ ጌታን ብዬ አላፈርኩ እርሱን ብዬ ጨመረ ምሥጋናዬ (2x) ጨመረ ምሥጋናዬ ተሰርቶልኝ ስራዬ ሃዘን ሄዷል ከላዬ ቤቴን ሞላው ደስታ ልዘምር ለዚህ ጌታ (2x) ልዘምር ለዚህ ጌታ (8x)