በምሥጋና ወደመቅደሱ እገባለሁ ከልቤ ሆኜ እቀኛለሁ ያከበረኝን ሰው ያረገኝን አምላኬን አመልከዋለሁ በምሥጋና ወደመቅደሱ እገባለሁ ከልቤ ሆኜ እቀኛለሁ የወደደኝን አዎ የሞተልኝን ኢየሱሴን አከብረዋለሁ ኢየሱስ ኢየሱስ (4x) ኢየሱስ ኢየሱስ (4x) ኢየሱሴ ክብሬ ማረጌ ኢየሱሴ የአብ ስጦታ ኢየሱሴ ነህ ዝርግፍ ጌጤ ኢየሱሴ ውበቴ ጌታ ኢየሱሴ የምትወደድ ኢየሱሴ ፍቅር እኮ ነህ ኢየሱሴ አሳዳጊዬ ኢየሱሴ ይቧረክ ስምህ (2x) የሚያንኳኳ መልስ ሽቶ ማን አፈረ አንተን ጠርቶ ማን አፈረ አንተን ጠርቶ (2x) ልመናውን ሰማህለት ሸክሙን አንተ ወሰድክለት ሸክሙን አንተ ወሰድክለት (2x) ተደንቂያለሁ በማዳንህ ተነገሮ አያልቅም ድንቅ ስራህ መፍቻው ተገኝቶ የእንቆቅልሹ ሌላ ሰው ሆኗል ዮሴፍ ትንሹ ተዐምር ነው ስራህ ጌታዬ ከፍ በል በምሥጋናዬ ድንቅ ነው ስራህ ጌታዬ ከፍ በል በምሥጋናዬ ከፍ በል በምሥጋናዬ (2x) የቱን ትቼ የቱን ላውራ ኢየሱሴ የአንተን ስራ (2x) ባይመጥንም ምሥጋናዬ ይኸውልህ አባብዬ (2x) ሰው የናቀውን የገፋውን መቼ ተውከው ብቸኛውን መቼ ተውከው ብቸኛውን (2x) አከበርከው በአደባባይ ትዕዛዝ ወጣለት ከሠማይ ትዕዛዝ ወጣለት ከሠማይ (2x) አይቻለሁኝ ስትረዳ ከጐኑ ስትሆን ለተጐዳ እጄን በእጆችህ ይዘህ መራህ ያልገመትኩትኝ ክብር አሳየኸኝ ማረጌ ክብሬ ኢየሱሴ ላምልክህ ከልብ ከነፍሴ ማረጌ ክብሬ ኢየሱሴ ላድንቅህ ከልብ ከነፍሴ ላምልክህ ከልቤ ኢየሱሴ ላምልክህ ከልብ ከነፍሴ ኢየሱሴ የመዳን ቀንዴ ኢየሱሴ መታመኛዬ ኢየሱሴ አንተ ነህ ውዴ ኢየሱሴ ወንድም ጋሻዬ ኢየሱሴ ምትክም የለህ ኢየሱሴ የፍቅር ምርጫዬ