Song Lyrics

ይሰራ

Yosef Bekele
Kidisina Le Egziabher
ለእግዚአብሔር የሚሳነው አለ ወይ የሚያቅተው አለ ወይ አለ ወይ ኧረ አለ ወይ ለኢየሱስ የሚሳነው አለ ወይ የሚያቅተው አለ ወይ አለ ወይ ኧረ አለ ወይ በፍፁም የለም አልሰማሁም ከትላንት ዛሬም አላየሁም እኔ የገባኝ አንድ እውነት የእግዚአብሔር ታላቅነት ይሰራል ዛሬም ይሰራል ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አምናለሁ እኔ አይቻለሁ ለአባቴ ሁሉ ቀላል ነው (2x) ለእግዚአብሔር ሁሉ ቀላል ነው ለእግዚአብሔር ሁሉ ቀላል ነው ለአባቴ ሁሉ ቀላል ነው ለጌታ ሁሉ ቀላል ነው አበቃ ከእንግዲህ ለተባለ ሁሉ ሲያኖር አይቻለሁ በሕይወት እንደቃሉ መቃብር ከፍቶ የሞተን ያስነሳል እኔ የማመልከው አምላኬ ይሰራል አምላኬ ይሰራል አምላኬ ይሰራል አባቴ ይሰራል አባቴ ይሰራል ይሰራል ዛሬም ይሰራል ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አምናለሁ እኔ አይቻለሁ ለአባቴ ሁሉ ቀላል ነው ለእግዚአብሔር ሁሉ ቀላል ነው ለእግዚአብሔር ሁሉ ቀላል ነው ለአባቴ ሁሉ ቀላል ነው ለጌታ ሁሉ ቀላል ነው ነፍሴን የፈጠረ ያበጀ ሥጋዬን ሕያው ያደረገኝ ሰጥቶ እስትንፋስን ይችላል ወይ ብዬ እንዴት ልጠርጥረው እኔ ልመን እንጂ ለጌታ ቀላል ነው ለጌታ ቀላል ነው ለጌታ ቀላል ነው ለአባቴ ቀላል ነው ለኢየሱስ ቀላል ነው ለሰው የማይቻል ለኢየሱስ ይቻላል (2x) ለሰው የማይቻል ለአባቴ ይቻላል ለሰው የማይቻል ለጌታ ይቻላል ለኢየሱስ ይቻላል ለኢየሱስ ይቻላል ለጌታ ይቻላል አዎ ይቻላል ይቻላል ይቻላል ኦሆ ይቻላል ይቻላል ሟርተኛው ቢያሟርት አይሁንለት ብሎ ሊያዘገይ ቢሞክር በረከቴን ታግሎ በአምላኬ ስም ሆኜ አሸንፈዋለሁ የኢየሱስ ስሙ ዛሬም ጉልበታም ነው ዛሬም ጉልበታም ነው ዛሬም ጉልበታም ነው ምሽግን ለማፍረስ ዛሬም ጉልበታም ነው ነፋስ ባይታይ ደመና ጭው ያለ ቢሆን በረሃ እኔስ አባቴን አውቀዋለሁ እንደሚሰራ አምነዋለሁ አያለሁ ተዐምር ሰርቶ ተዐምር ሰርቶ ጐዶሎው ሁሉ ሞልቶ ሁሉ ሞልቶ አያለሁ ተዐምር ሰርቶ ተዐምር ሰርቶ የሌለው ሁሉ ሞልቶ ሁሉ ሞልቶ አያለሁ ተዐምር ሰርቶ ጐዶሎው ሁሉ ሞልቶ አያለሁ ተዐምር ሰርቶ የሌለው ሁሉ ሞልቶ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection