Song Lyrics

ትልቅ ነህ

Yosef Bekele
Kidisina Le Egziabher
ዝናህን ላውራ ኦሆሆሆ ታላቅነትህን ስላንተ ዝና አውርቼ አልጠግብም ብናገር ብናገር (2x) ኦ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ አንተ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ ኦ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ አንተ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ ትልቅ ነህ (4x) ትልቅ ነህ (4x) ቀና ብዬ ሠማዩን ሳይ ጨረቃዋን ከዋክብቱን ሳይ አሻቅቤ ተራራውን ሳይ ባሕሩን ውቅያኖሱን ሳይ አፈጠጠሩ ይገርመኛል አቤት ውበቱ ይደንቀኛል ጌታዬ የአንተን ትልቅነት ያሳየኛል አመልክሃለሁ እጆቼን አንስቼ አመልክሃለሁ ፊትህ ተደፍቼ አመልክሃለሁ ክብሬን ሁሉ ትቼ አመልክሃለሁ ወድጄ ፈቅጄ ኦ አንተ ታላቅ ነህ እኔም አላውቅህም (2x) ኦ አንተ ታላቅ ነህ እኛም አናውቅህም (2x) የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ የማትመረመር መርማሪ ጥበብህን ዕውቀትህን ማን ያውቀዋል ፍርድህም ከማስተዋል ሁሉ ይልቃል ኦ ለመንገድህ ፍለጋ የለው አደራረግህ እጅግ ጥልቅ ነው አቤቱ ስራህ ከአይምሮ በላይ ነው ትልቅ ነህ (4x) ትልቅ ነህ (4x) ውሆችን በእፍኝህ የሰፈርህ ተራሮችን በሚዛን የመዘንህ ሠማዩን በስንዝር የለካህ የምድርን አፈር ሰብስበህ የያዝህ ሁሉን ስትሰራ ማን አማክሮሃል የፍርድን መንገድ ማን አስተምሮሃል አቤት ጥበብህ ከሁሉ ይልቃል ኦ አመልካህለሁ አሃ አመልክሃለሁ አሁ አመልክሃለሁ ጌታ አመልክሃለሁ ኦ አመልካህለሁ አባ አመልክሃለሁ አሁ አመልክሃለሁ ጌታ አመልክሃለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection