Song Lyrics

ይሆናል

Yosef Bekele
Kidisina Le Egziabher
የቀድሞውን ነገር አላስብም አሮጌው ሁሉ አልፏል ሁሉ አልፏል ተፈጠመ ያየጥንቱ ታሪክ ዘመን መጥቶልኛል የቀድሞውን ነገር አላስብም አሮጌው ሁሉ አልፏል ሁሉ አልፏል የእንባው ጊዜ ታሪክ ሆኖ ሊቀር ቀን ተቀጥሮለታል እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ እርሱንም አሁን አበቅለዋለሁ ያለኝ ጌታ ያለኝ ጌታ የተናገረኝን ያደርገዋል ያደርገዋል አምነዋለሁኝ አምነዋለሁኝ (4x) ይሆናል አዲስ ነገር አያለሁ አንድም አይቀር ይሆናል አዲስ ነገር አያለሁ አንድም አይቀር የተናገረኝ ጌታ ሰው አይደል ሚያመነታ ቃል ወጥቷልና ከእርሱ ያደርገዋል ንጉሡ ይሆናል ይሆናል ጌታ ያለው ይሆናል ይሆናል ይሆናል እርሱ ያለው ይሆናል (አዲስ ነገር ይሆናል አዲስ ነገር አዲስ ነገር) ሽንፈት አላወራም ድል አለ ከፊቴ ኃይል የእግዚአብሔር ነው ይሄ ነው ትምክቴ የነሃሱ ደጃፍ አውቆ ይከፈታል እግዚአብሔር ሲነሳ ኧረ ማን ይቆማል ይሆናል ይሆናል ጌታ ነው ይሆናል ይሆናል ይሆናል እርሱ ያለው ይሆናል ዐይኖች ያላዩትን ጆሮም ያልሰማውም ከሰዎች ዘንድ ከቶ ያልተገመተውን እንግዳ ነገርን አምላኬ ያደርጋል አዲስ አዲስ ነገር በሕይወቴ ይሆናል ቃል አለኝ ቃል አለኝ እኔ ይሰራል አያለሁ በዐይኔ ቃል አለኝ ቃል አለኝ እኔ ይሰራል አያለሁ በዐይኔ አያለሁ በዐይኔ (4x) ምድረ በዳ ቢሆን አንተ ያለህበት አትፍራ ወንድሜ ጽና በቆምክበት ጻድቁ እግዚአብሔር እንዴት ይጥልሃል ታሪክን ገልብጦ ገና ያቆምሃል ተስፋ የሰጠህ የታመነው የታመነው ሁሉን ይሰራል ኤልሻዳይ ነው ኤልሻዳይ ነው ተስፋ የሰጠህ የታመነው የታመነው ሁሉን ይሰራል ኤልሻዳይ ነው ኤልሻዳይ ነው አምናለሁ እርሱ ታማኝ ነው ጌታዬ እርሱ ታማኝ ነው ይሰራል እርሱ ታማኝ ነው ያደርጋል እርሱ ታማኝ ነው ምድር ብታልፍ ሠማይ ቢያልፍ ቃሌ ግን አያልፍም ያለው ጌታ እኮ ነው ጌታ እኮ ነው (2x) ኧረ የምን ሥጋት ለምን ፍርሃት ሁሉን ቻይ አምላክ አለኝ አባት ትዕዛዝ ከሠማይ ከአምላኬ ወጥቶ እንዴት ይሆናል አልልም ከቶ አልልም ከቶ (4x) ቃል አለኝ ቃል አለኝ እኔ ይሰራል አያለሁ በዐይኔ ቃል አለኝ ቃል አለኝ እኔ ይሰራል አያለሁ በዐይኔ አያለሁ በዐይኔ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection