ከአንተ ጋራ ኖሬ አንተን አስከብሬ ፍሬን እንዳፈራ ነበረ ምኞትህ ያሁሉ ልፋትህ እኔን ስትሰራ ቅጠሉ እንዳማረ ግን ፍሬ እንደሌለው በለስ ሆኛለሁ ጥቂት ታገሰኝ አንድ እድል ስጠኝ ፊትህ ወድቄያለሁ እንዳትተወኝ እማጸናለሁ ከተውከኝማ ወዴት እሄዳለሁ (2x) ባጠፋ እንኳ ቆንጥጠህ መልሰኝ ብበድልህ እንኳ ገስጸህ መልሰኝ የእኔ ጌታ ያለአንተ ማን አለኝ ድንጋዩን ልቤን ባክህ አውጣልኝ አባ እባክህ አውጣልኝ አዲስን መንፈስ በውስጤ አኑርልኝ ጌታ በውስጤ አኑርልኝ ድምጽህን ስሰማ አው አልሁን እልኸኛ ቸል ብዬ እንዳልጠፋ አባ እባክህ አንቃኛ እባክህ አንቃኛ (2x) የሰጠኸኝን ያንን አደራ ያንን መክሊት . (1) . ነክቼ እንድጠብቅህ ብዙ አትርፌበት ምንም ሳልሰራ እንደቀበርኩት ምጻትህ ቀርቧል አንቃኝ ጌታዬ ከስንፍናዬ ኋላ እንዳልጣል ዝም እንዳትለኝ እማጸናለሁ ዝም ካልክማ እኔ እፈራለሁ (2x) አባ አድነኝ ከቁጣህ አድነኝ አድነኝ ኢየሱስ አድነኝ ለጠፊው ዓለም ስጥር ስለፋ ጊዜዬ አልቆ ሠማያዊውን የዘለዓለሙን ልቤ ዘንግቶ ኃይሌ ተሟጦ ዘይቴ አልቆ ባዶ ሆኛለሁ ማረኝ አባቴ ገባኝ ጥፋቴ እመለሳለሁ እኔን ለምኞቴ አትስጠኝ ጌታዬ አትስጠኝ ጌታዬ እኔን ለሥጋዬ አትስጠኝ አባዬ አጽጠኝ አባዬ እግዚአብሔርን መፍራት ጠፍቶ የለም ወይ ምኞቱን የሚያረግ ሞልቶ የለም ወይ ባክህ በዚህ ዘመን አባ አስተዋይ አድርገኝ ወደ ጽድቅ ጐዳና አሃ እግሬን መልስልኝ አድነኝ አባ አድነኝ ኢየሱስ አድነኝ ጌታ አድነኝ አን