Song Lyrics

ቤተክርስቲያን

Yosef Bekele
Balewuletaye Geta
አዝ፦ ቤተክርስቲያን ሙሽራይቱ ሙሽራሽ ሊመጣ ጊዜው አይደለም ወይ አጊጠሽ ጠብቂ ተዘጋጂ ቶሎ ሙሽራሽ ይመጣል መላዕክት አስከትሎ በመላዕክት ታጅቦ ኦሆ የቀድሞ ፍቅርሽን አድሺ በጊዜ ከአንቺ ይወገዱ ድካም ድንዛዜ ንቂ መብራት አብሪ ተዘጋጂ ፈጥነሽ ጠብቂው ኢየሱስን ጌጠኛ ልብስ ለብሰሽ ያማረ ልብስ ለብሰሽ አዎ በራድ ወይም ትኩስ ከቶም አይደለሽ እስካሁን ኖረሻል እንዲያው ለብ ብለሽ ትምክጽህን ጣዪ አትበይ ሁሉ አለኝ ኋላ እንዳታጪ ሊመጣ ያለውን ሊገለጥ ያለውን አዎ አዝ፦ ቤተክርስቲያን ሙሽራይቱ ሙሽራሽ ሊመጣ ጊዜው አይደለም ወይ አጊጠሽ ጠብቂ ተዘጋጂ ቶሎ ሙሽራሽ ይመጣል መላዕክት አስከትሎ በመላዕክት ታጅቦ ኦሆ ከፈሰሰልሽ ደም ጉድፍሽኝ አጥሪ ቀን ሳለ በጊዜ ራስሽን መርምሪ ቁም ግዢ ከጌታ ዓይንሽ ይከፈታል የጐደለሽ ሁሉ ያኔ ይታይሻል ያኔ ይታይሻል አዎ ኩራዝሽን አብሪ ዘይቱንም ግዢ ምንም እንዳይጐድልሽ ትጊ ተጠንቀቂ የምትጠብቂው ሙሽራ ይመጣል አታፍሪም ዘለዓለም እርሱም ያከብርሻል ከፍም ያደርግሻል አዎ ድል ለነሣው ከጌታ ጋር በዙፋን ላይ ይቀመጥ ዘንድ ይሰጠዋል መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ [1]
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection