አዝ፦ ላመስግነው ጌታን ላመስግነው ላመስግነው ውዴን ላመስግነው የረዳኝን ኢየሱስ ያገዘኝን ያቆመኝን አምላኬን ሰው ያደረገኝን ላመስግነው ዛሬም አቻም የለውም ቢያወድሱት እርሱስ ማይጠገብ ነው ላመስግነው የኃጢአቴን ቀንበር በላዬ ያለውን ሰበረው ከላዬ ቀና አደረገኝ ጌታዬ ቀደደው የመርገም ጨርቄን አራቀው ውዴ አበሳዬን አነጻኝ ጌታ በደሙ በልቤ ሞላ ሰላሙን ላመስግነው አዝ፦ ላመስግነው ጌታን ላመስግነው ላመስግነው ውዴን ላመስግነው የረዳኝን ኢየሱስ ያገዘኝን ያቆመኝን አምላኬን ሰው ያደረገኝን ላመስግነው ዛሬም አቻም የለውም ቢያወድሱት እርሱስ ማይጠገብ ነው ላመስግነው ዙሪያዬን ከቦኝ ጠላቴ ሚረዳኝ ባጣሁኝ ጊዜ በጭንቄ ሳለሁ ደረሰ እምባዬን ከዓይኔ አበሰ አሰበኝ ከአሪያም አምላኬ ጋሻዬ ሆነ ምርኩዜ ረገጠው ያስጨነቀኝን አሳደደው ያሳደደኝን ላመስግነው አዝ፦ ላመስግነው ጌታን ላመስግነው ላመስግነው ውዴን ላመስግነው የረዳኝን ኢየሱስ ያገዘኝን ያቆመኝን አምላኬን ሰው ያደረገኝን ላመስግነው ዛሬም አቻም የለውም ቢያወድሱት እርሱስ ማይጠገብ ነው ላመስግነው ምስቅልቅል ያለው ሕይወቴን የባዘነችውን ነፍሴን ኢየሱሴ ደርሶ አጣፈጠው መራራውን ሕይወት ለወጠው ሙሉ አደረገኝ ወዳጄ አወጣኝም ከኩነኔ እንክፈለው ለዚህ ጌታ ላክብረው ክብሬን በዕልልታ ላመስግነው አዝ፦ ላመስግነው ጌታን ላመስግነው ላመስግነው ውዴን ላመስግነው የረዳኝን ኢየሱስ ያገዘኝን ያቆመኝን አምላኬን ሰው ያደረገኝን ላመስግነው ዛሬም አቻም የለውም ቢያወድሱት እርሱስ ማይጠገብ ነው ላመስግነው ሰው የጠላውን ሃሳቢ የተገፋውን ሰብሳቢ ለቸገረው ፈጥኖ ደራሽ ለሚያነባ እምባውን አባሽ አንተ ነህ እውነተኛ ወዳጅ ማትለይ ሁሌም ማትሰለች ቢመኩብህ ታስመካለህ ኢየሱሴ አንተ ታኮራለህ ላመስግንህ አዝ፦ ላመስግነው ጌታን ላመስግነው ላመስግነው ውዴን ላመስግነው የረዳኝን ኢየሱስ ያገዘኝን ያቆመኝን አምላኬን ሰው ያደረገኝን ላመስግነው ዛሬም አቻም የለውም ቢያወድሱት እርሱስ ማይጠገብ ነው ላመስግነው