Song Lyrics

በማለዳ ምሥጋና

Yosef Bekele
Balewuletaye Geta
አዝ፦ የሚረዳኝ የለም ከአንተ ሌላ የውስጥ ብሶቴን ጭንቄን ሚያሟላ እድል ፈንታዬ አንተው ነህና አዋይሃለሁ አጫውትሃለሁ ማን አለኝ ከአንተ ሌላ (2x) ዞሬያለሁኝ በዓለም ተስፋ አገኝ መስሎኝ በከንቱ ዘመኔን እንዲያው ጨረስኩኝ የምታዛልቀኝ አንተው ብቻ ነህ ተረድቻለሁ ና እምባዬን አብስ ተስፋዬን አድስ ከማህጸን ጀምሮ ተሸክመኸኛል እንደ ልጅ አባብለህ አሳድገኸኛል ከአንተ ወዲያ ለእኔ የለኝም የማውቀው ኧረ ፊትህ ወድቄ እማጸንሃለሁ ጌታ ጌታ የእኔ ማረፊያ ጌታ አለሁልህ በለኝና እስኪ ልረፍ ድምጽህን ልስማ ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ መጠጊያዬን አውቃለሁ አዝ፦ የሚረዳኝ የለም ከአንተ ሌላ የውስጥ ብሶቴን ጭንቄን ሚያሟላ እድል ፈንታዬ አንተው ነህና አዋይሃለሁ አጫውትሃለሁ ማን አለኝ ከአንተ ሌላ (2x) ወደ ቀኝ ወደ ግራ ተመለከትኩኝ ተስፋ የሚሆነኝ አንድም አጣሁኝ መሸሸጊያዬ ለእኔ መድሃኒት ለነፍሴ ጌታ ና ከእስራት ፍታኝ ልጄ ነህ በለኝ ብዙ ነገር አለኝ እኔስ የማጫውትህ የልቤን የውስጤን ሁሉንም ልንገርህ ኢየሱስ ነፍሴ በእጅህ ናት መላው አካላቴ ፈቃድህ ይሁንልኝ ያልከው በሕይወቴ ጌታ ጌታ የእኔ ማረፊያ ጌታ አለሁልህ በለኝና እስኪ ልረፍ ድምጽህን ልስማ ከአንተ ወዴት እሄዳለሁ መጠጊያዬን አውቃለሁ አዝ፦ የሚረዳኝ የለም ከአንተ ሌላ የውስጥ ብሶቴን ጭንቄን ሚያሟላ እድል ፈንታዬ አንተው ነህና አዋይሃለሁ አጫውትሃለሁ ማን አለኝ ከአንተ ሌላ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection